Archive

Author: Editor

 የኬንያ አየር መንገድ ወደኢትዮጵያ በሳምንት ሶስት ቀናት ያደርግ የነበረውን በረራ ወደሰባት ማሳደጉን አስታወቀ

(ዘ-ሐበሻ ) የኬንያ አየር መንገድ ወደኢትዮጵያ በሳምንት ሶስት ቀናት ያደርግ የነበረውን በረራ ወደሰባት ማሳደጉን አስታወቀ፡፡ ይህንን ውሳኔ ያደረገውም የመንገደኞች ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ በማደጉ እንደሆነ ገልጿል፡፡ የኬንያ አየር መንገድ በሳምንት ተጨማሪ አራት በረራዎችን እያደረገ ያለው በርካታ አገራት ዜጎቻቸውን ከኢትዮጵያ የማስወጣት እንቅስቃሴ ላይ በመሆናቸው ነው፡፡ አየር መንገዱ በዚህ እድል ለመጠቀምና የመንገደኞችን ቀልብ…

ቆቦ ላይ የተቆረጠው ሕወሓት ሃራንም አጣ | አሁን ሎጂስቲክ ከመቀሌ ማምጣት የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል | ሕወሓት በበርሐ ስላሴ ሚኒሻዎች ላይ ዲሽቃ ሲወረውር ዋለ

የሰሜን ወሎ አርሶ አደር ታጣቂዎች በተለይም የድሬ ሮቃና ሶድማ አርሶ አደር ታጣቂዎች በጀግንነት እየተዋጎ የሕወሓትን ኃይል እየመቱ መሆኑን በትናንትናው ዕለታዊ ዜና መዘገባችን አይዘነጋም። እነዚህ አርሶ አደሮች ልክ እንደቆቦና ዞብል ሁሉ ሃራ ላይ የነበረውን የሕወሓት ኃይል ደም ሰሰው ከተማዋን በቁጥጥራቸው ስር ማስገባታቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጭ ገልጹ። ከዞብል የተነሱ አርሶ አደሮች የኢትዮጵያ አየር…

ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

የብልጽግና መንግሥት ሥልጣን ከያዘበት ከመጋቢት 2010 ዓ.ም. ጀምሮም ሆነ በቅርቡ “አዲስ መንግስት” “አዲስ ምዕራፍ” እየተባለ ከሚነገርለት ከመስከረም 24/2014 ዓ.ም. በኋላ ባለው ጊዜ መንግስት ሊሠራቸው የሚገቡ ዋንኛ ተግባሮችን ሲያከናውን አልታየም፡፡ እነዚህም የሃገርን ሉዓላዊነት ማፅናት፣ የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ማስከበር፣ የሕግ የበላይነትን ማስፈን እና የሃገርን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ሕይወት ማረጋጋት ናቸው፡፡ ብልጽግና ከነዚህ አንዱንም…

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከጋዜጠኞች ጋር አስገራሚ ፍጥጫ ገጠማቸው

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ቃል አቀባዩ ኔድ ፕራይስ ትላንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ የሰብአዊ እርዳታው እንቅስቃሴ መገደብ እንደሌለበትና እርዳታ የጫኑ መኪናዎች ወደትግራይ ክልል ሊተላለፉ እንደሚገባ አበክረው አሳስበዋል፡፡ እነዚህ መኪናዎች እንዲጓጓዙ የኢትዮጵያ መንግስት መፍቀድ እንዳለበትም ጠይቀዋል፡፡ ስለእርዳታው ሁኔታ ተጠይቀው ይህንን መሰል ምላሽ በመስጠት ላይ የነበሩት ኔድ ፕራይስ ቀጠል አድርገው አጀንዳ በመቀየር በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ…

ከእንግሊዝ ጦር ሀይል የተውጣጡ ወታደሮች ብሪታኒያዊያንን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት በምስጢር ኬንያ መግባታቸው ተዘገበ

Photo: File (ዘ-ሐበሻ ዜና) ቱ ራፋይልስ ከተሰኘው የእንግሊዝ ጦር ሀይል የተውጣጡ ወታደሮች ብሪታኒያዊያንን ከኢትዮጵያ ለማስወጣት በተጠንቀቅ ቆመው እየተጠባበቁ መሆኑን ዘ ታይምስ የተሰኘው ጋዜጣ ዛሬ ባሰራጨው መረጃ ገልጿል፡፡ እነዚህ ቁጥራቸው ከአንድ መቶ በላይ የሆኑ ወታደሮች በአሁኑ ወቅት በጎረቤት አገር ኬንያ በምስጢር መስፈራቸውን ጋዜጣው ወታደራዊ ምንጮቹን ዋቢ አድርጎ አስረድቷል፡፡ ኬንያ የገቡት እነዚህ ወታደሮች…

“በአሜሪካ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን መራጮች በቨርጂኒያ ምርጫ ለባይደን መልእክት አስተላልፈዋል” – ዘ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዘ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ‹‹በአሜሪካ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን መራጮች በቨርጂኒያ ምርጫ ለባይደን መልእክት አስተላልፈዋል›› ሲል ዘግቧል፡፡ ጋዜጣው በቨርጂኒያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መራጮች ለምን ለዩንግኪን ድምፃቸውን ሊሰጡ ቻሉ? ይህስ እንዴት በሌሎች ቦታዎች ለዲሞክራቶች ችግር ሊፈጥር ይችላል? በማለት ሰፊ ትንታኔ አስነብቧል፡፡ በትንታኔው ግርማ መኮንን የተባለውን ኢትዮጵያዊ ጠቅሶ ይህ ሰው ራሱን የዲሞክራቶች ታማኝ…

ሊዝ ትሮሴል በኢትዮጵያ ጉዳይ ጋዜጣዊ መግለጫ አወጡ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር ቃል አቀባይ ሊዝ ትሮሴል በኢትዮጵያ ጉዳይ ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ በመግለጫቸው ባለፉት ሁለት ሳምንታት በኢትዮጵያ ውስጥ የተጣለውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተገን በማድረግ በአዲስ አበባ፣ በጎንደር፣ በባህር ዳርና ሌሎችም አካባቢዎች መጠነ ሰፊ እስርና ፍተሻ እየተከናወነ መሆኑ ድርጅታቸውን እንዳሳሰበው ገልፀዋል፡፡ ይህ ከሚከናወንባቸው ውስጥ…

በአዲሱ መጠሪያው ሜታ የተባለው ፌስ ቡክ ለኢትዮጵያ ተጠቃሚዎቹ አዲስ መመሪያ አውጥቷል

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአዲሱ መጠሪያው ሜታ የተባለው ፌስ ቡክ ለኢትዮጵያ ተጠቃሚዎቹ አዲስ መመሪያ አውጥቷል፡፡ ‹‹ኢትዮጵያ የግጭት ስጋት ያለባት አገር እንደመሆኗ መጠን ቅድሚያ ከምንሰጣቸው አገራት ተርታ አስቀምጠናት ቆይተናል›› ሲል የጀመረው መመሪያው ባለፉት ሁለት አመታትም በኢትዮጵያ ውስጥ ጥላቻንና ለግጭት የሚያነሳሱ ይዘቶችን ለመቀነስ ከፍተኛ ወጪ ሲያደርግ የቆየ መሆኑን አስታውቋል፡፡ አሁን ደግሞ ሁኔታው እየተባባሰ በመምጣቱ…

የአሜሪካ ስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) አስገራሚ ትንበያ በኢትዮጵያ ላይ አወጣ

(የዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) ከሚገኝ መረጃ በየጊዜው የሚወጣው ‹‹ኢንሴኪዩሪቲ ኢንሳይት›› ዛሬ ኢትዮጵያን የተመለከተ ትንታኔና ትንበያውን አቅርቧል፡፡ ትንታኔውን የጀመረው በአዲሱ የተቃዋሚዎች ጥምረት ወደፊት መግፋት የኢትዮጵያ መንግስት ጫና ውስጥ መግባቱን በመግለፅ ሲሆን በህወሀትና በኦነግ ሸኔ እየተደረገ ያለው ውጊያ አላማው በፍጥነት ሁሉንም ወደአዲስ አበባ የሚያስገቡ መንገዶች መዝጋት እንደሆነ አስታውቋል፡፡ በዚህም መንግስት…

ሚሌን ለመዘጋት ለወራት እየሞከረ መንገዱ አቅሙ ያልቻለው ሕወሓት ዛሬም ተመሳሳይ ሽንፈት እንደገጠመውና በርካታ ኃይሉም እየተማረከ መሆኑ ተገለጸ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያን ጉሮሮ በቀናት ውስጥ እዘጋለሁ በሚል የኢትዮ ጅቡቲ መስመር የሆነውን ሚሌን ለመዘጋት ለወራት እየሞከረ መንገዱ አቅሙ ያልቻለው ሕወሓት ዛሬም ተመሳሳይ ሽንፈት እንደገጠመውና በርካታ ኃይሉም እየተማረከ መሆኑ ተገለጸ። በአሸባሪነት የተፈረጀው ሕወሓት ወደ ሚሌ በባቲ መስመር እንዲሁም በጭፍራ በኩል በ2 አቅጣጫ ቆርጦ ለመሄድ ያለ የሌለ ሃይሉን ለወራት ገብሯል። ለደጋፊዎቹም ትናንት…