Archive

Category: News

የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ በትናንትናው ዕለት በኤርትራ መንግስት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አወገዘ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ እንደነበር በመጥቀስ ተቃውሞውን ጀምሯል። ስለዚህም የአሜሪካ መንግስትም የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ መንግስት ጠይቆ ምክንያቶችን ዘርዝሯል። 1. “ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረሰውን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ ሉዓላዊት…

የዘ-ሐበሻ የዕለቱ 9 አጫጭር ዜናዎች

1. የዋግ ህምራ ሰቆጣ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ ብፁእ አቡነ በርናባስ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ተሰማ፡፡ አደባባይ ሚዲያ እንዳስታወቀው ብፁእነታቸው ታፍነው ስለመወሰዳቸው ቢነገርም ምንም ችግር እንዳላጋጠማቸው ከምንጮቹ ሰምቷል፡፡ በአካል ጳጳሱን ያገኙ ሰዎችን ምስክርነት ማግኘቱንም አስረድቷል፡፡ ብፁእነታቸው የድጓ፣ የቅኔ፣ የዝማሬ መዋስት፣ የሀዲስ ኪዳንና የብሉይ ኪዳን ሊቅና የትህትና መምህር እንዲሁም የፀሎት አባት መሆናቸውንም…

በዳውንት ወደ በታች ጋይንት ቆርጦ ሊመጣ የነበረው የሕወሓት ኃይል ተመታ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) አሸባሪው እና ወራሪው የሕወሓት ኃይል በጋሸና መስመር ያለውን የኢትዮጵያን ኃይሎች አሰላለፍ ለማዛባት በዳውንት በኩል ቆርጦ ወደ ታች ጋይንት ለመግባት ሙከራ እያደረገ መሆኑን ከቀናት በፊት በዘ-ሐበሻ ዜና ዘግበን ነበር። ዛሬ የደቡብ ጎንደር የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ይርጋ ሲሳይ ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ይህን አረጋግጠው ከሰሞኑ በዳውንት መስመር አድርጎ በታች…

“በዚህ ጦርነት ከአማራ ህዝብ ጋር ሊያጫርሱን ነው፤ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው”

ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንቅ እንቅ እያደረገው፣ በፍርሃት ማንበብ እየተጨነቀ፣ ፈራ ተባ እያለ፣ አንዳንዴም ደፈር ለማለት እየሞከረ የተሰጠውን ንባብ እንደምንም ጨርሷታል። ከአማራ ህዝብ ሱዳን ይሻለኛል ሲል የነበረው ደብረጽዮን ዛሬ ደግሞ “በዚህ ጦርነት ከአማራ ህዝብ ጋር ሊያጫርሱን ነው፤ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው” በሚል የአማራ ተቆርቋሪ ሆኖ ቀርቧል። ወደ ወሎ ሰላማዊ ሕዝብ መድፍ እየወረወረ…

የኢትዮጵያ አየር ኃይሎች በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ የሚገኝ ወታደራዊ ስትራቴጂካዊ ቦታን ማውደማቸው ተገለጸ

የተመረጡ ወታደራዊ ኢላማዎችን ብቻ በተሳካ ሁኔታ በመምታታቸው የአየር ስናይፐሮቹ የሚል ስያሜ የወጣላቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይሎች በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ የሚገኝ ወታደራዊ ስትራቴጂካዊ ቦታን ማውደማቸው ተገለጸ። የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዛሬ ጥቅምት 18/2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ በመቐለ የተመረጡ የአሸባሪ ህወሓት ወታደራዊ ቤዞችን የመታው። መቐለ ከተማ እና ዙርያዋ ከደርዘን በላይ የአሸባሪ ህወሓት ወታደራዊ…

3 አጫጭር ዜናዎች

  በሰሜን ጎንደር ግንባር ከፍተኛ ሽንፈትን የተከናነበው አሸባሪውና ደም መጣጩ ምግበ ኃይለ የሚመራው የሕወሃት ኃይል ሽንፈቱን ለማካካስ ትናንት ምሽት ወደ ደባርቅ መስመር መድፍ ከርቀት ሆኖ መተኮሱን የዘ-ሐበሻ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል። እቅዱ ሰላማዊ ሰዎችን ለመምታትና ለመረበሽ ቢሆንም በዚህ ሰሜን ጎንደር ግንባር ከ16 ሺህ በላይ የሕወሓት ታጣቂን የረፈረፉት የሰሜን ጀግኖች ተክሱን ከቁብ…

ሕወሓት የሚተማመንበት አጋዚ ቁጥር 2 ኮማንዶ ተመታ

  ሕወሓት እተማንበታለው እያለ በስፋት ስለጀግንነቱና ገድሉ ሲለፍፍለት የነበረው አጋዚ ቁጥር 2 ብርጌድ ኮማንዶ ወደ ሐይቅ ከተማ እየተጠጋ በነበረበት ሰዓት በኢትዮጵያ ኃይሎች አከርካሪው ተመታ። በዚህም የአጋዚ ብርጌድ ኮማንዶዎች መካከል አብዛኛዎቹ ሙትና ቁስለኛ መሆናቸውን የሚናገሩት የመከላከያው ምንጭ ወደ ጊራና እና ወረባቢ የቀሩት በፍርሃት እያዝረጠረጡ መሸሻቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በዚያ አካባቢ ተመልሰው ሊደራጁ…

ሕወሃት ወደ ደሴ ለመግባት ኃይሉን ለማጠናከር ከደላንታ እያጓጓዘው የነበረው ኃይል ሙሉ በሙሉ ተመታ | ቦሩ ስላሴ የነበረው የተሽከርካሪና የሰው ክምችት ወድሞበታል

  አሸባሪውና ወራሪው የሕወሓት ኃይል በደሴ አቅራቢያ ያለው ኃይሉ እጅጉን በመመናመኑ ይህንን ኃይሉን ለማጠናከር ከደላንታ አካባቢ እያመጣው የነበረው ተጨማሪ ኃይል መንገድ ላይ እንዳለ በድሮን በተወሰደበት እርምጃ ሙሉ በሙሉ መደምሰሱ ተሰማ። ሕወሓት በደላንታ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት እንደነበረው፤ በተለይም የደላንታ አንዳንድ አካባቢዎችን አለ ውጊያ መቆጣጠሩን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን ከዚህ አካባቢ ያለው…

በየት በኩል ሐይቅ እንደገቡ ያልታወቀ 19 የሕወሓት ታጣቂዎች ውስጥ 18ቱ ተደመሰሱ | ሆኖም ሃይቅ ልዩ ትኩረት ይፈልጋል | የአካባቢው ነዋሪ ቤቱን ጥሎ መሄዱን ሊያቆም ይገባል

  በየት በኩል ወደ ሐይቅ ከተማ እንዳልገቡ ገና እየተጣራባቸው ያሉ 19 የሕወሓት ታጣቂዎች መካከል 18ቱ መደምሰሳቸውን የዘ-ሐበሻ የመከላከያው ምንጭ አስታወቁ። ሆኖም ግን የአካባቢው ነዋሪ ሐይቅን እየለቀቀ እየተሰደደ መሆኑ ለሕወሓት ዝርፊያና መስፋፋት ጥሩ ዕድል ሊሆን እንደሚችል ምንጩ አክለዋል። በሐይቅ ቁልቋሎ፤. አሚናምባ እና ቀጤ አካባቢ የመጣው የጁንታው ኃይል ጋር ውጊያ እየተካሄደ እንደሆነ…

ሕወሓት ደሴን ለመቆጣጠር እየገበረ ያለው ሕዝብ ብዛት የትግራይን እናት ካለ ልጅ የሚያስቀር ነው ተባለ | ጠዋት ላይ ህወሓት ሰርጎ በመግባት ይስማኖ አካባቢ ሚኒሻው ላይ ተኩስ ከፍቶ ነበር | ወዲያው ተጠራርጎ ተደምስሧል የቀረው ወደ አላንሻ ሸሽቷል | ወደ ደሴ 5 ጊዜ መድፍ የጣሉት አስተኳሾች በድሮን ተመተው በእሳት ተጠባብሰው ተደምሰሰዋል

  አሸባሪውና ወራሪው የሕወሓት ኃይል ደሴን ለመቆጣጠር ዛሬም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የትግራይ ተወላጆችን እየማገደ ነው። ትግራይ በዚህ ዓይነት ከጊዜ በኋላ ወጣት አልባ መሆኗ የማይቀር ከመሆኑም በላይ የትግራይ እናቶችንም ካለ ጧሪ ቀባሪ የሚያስቀር እርምጃ ሕወሓት እየወሰደ ነው። የዘ-ሐበሻ ምንጭ እንደሚሉት ሕወሓት ትናንት ምሽቱን የደሴን ሕዝብ ለማሸበር ከርቀት ከባድ መሳሪያዎችን ተኩሰዋል። ትናንት…