ህልዉናችን የሚረጋገጠዉ በዋነኛነት በዉስጣዊ ሁኔታችን ነዉ!!

ከቹቹ አለባቸው
ከሰሞኑ አሜሪካ በታዋቂ የተማሩና ወታደራዊ ሊህቃኖቿ አማካኝነት፣ ህወሀትን ለማዳን ሲባል ወደ ኢትዮጵያ ጦር የማስገባት ፍላጎት እንዳላት አሰነግራለች። ይሄ ነገር የኢትዮጵያን ህዝብ የልብ ትርታ ለማዳመጥ መሆኑን አላጣነዉም።
ቹቹ አለባቸው
እዚህ ላይ የምንገነዘበዉ እዉነታ ቢኖር አሜሪካ ህወሀትን ለማዳን “ሲኦል ድረስ ለመዉረድ” የወሰነች መሆኑን ነዉ። አሁን ጥያቄዉ አሜሪካ ህወሀትን ለማዳን ይሄንን ያክል ከወሰነች እኛ ኢትዮጵያዊያን አገራችንና መንግስታችንን ለመታደግ እስከምን ድረስ መወሰን አለብን? የሚለዉ ነዉ። ይሄ ጥያቄየ የህወሀት ተቀላቢ የማራ ወንድምና እህቶቸን አይመለከትም፤ምክንያቱም የነሱ ፍላጎት ከአሜሪካኖቹ የተለየ አይደለምና። ስለሆነም የኔ ጥያቄ የህወሀት መራሽ መንግስት በዝች ምድር እንዳይከሰት ለሚመኙትና ለሚሰሩት ብቻ መሆኑ ይታወቅልኝ።
በጠዋቱ ፅሁፌ አቋሜን ግልፅ እንዳደረግኩት ፣አሁን ባለዉ ሁኔታ ለአማራ ህዝብ በዶ/ር አብይ የሚመራዉ መንግስት የተሻለዉ አማራጭ ነዉ። ምክንያቱም ይህ መንግስት ሄደ ማለት ህወሀት መራሽ መንግስት በቦታዉ ተተካ ማለት ነዉ። ይህ ከሆነ ደግሞ ለአማራ ህዝብ ትልቅ መከራ ነዉ። ይህ ሁኔታ መከራ የማይሆነዉ በባርነት መኖር ን መርጠዉ ለከረሙተሰ የህወሀት ተቀላቢዎች ነዉ።
ወደዋናዉ ጥያቄየ ልመለስ። አሜሪካና የህወሀት ተቀላቢወች ህወሀትን ለማዳን ይሄንን ያክል እርቀት ከሄዱ፣የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ደግሞ የአማራ ህዝብ አገሩንና መንግስቱን ከፍርሰት ለመታደግ የሚቀጥበዉ አቅምና ጊዜ ሊኖረዉ አይገባም እላለሁ። ትህነጋዊያንና አንዳንድ አማራዊ ወገኖች ይሄንን አቋሜን የግለሰብን ስልጣን ከማስጠበቅ ጋር እንደሚያያይዙት ይገባኛል። ጉዳዩ ግን አገርንና ህዝብን ከመታደግ አንፃር እንጅ የግለሰብን ስልጣን ከማስቀጠልና ካለማስቀጠል ጋር የሚታይ መሆን አልነበረበትም።
ሁላችንም እንደምናዉቀዉ ትህነግ የአገር መከላከያን በማጥቃቱ ምክንያት በመላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ የተወሰደበትን እና ዛሬም ድረስ እየተወሰደበት ያለዉን ምት ከዶ/ር አብይ ጋር ብቻ ተያይዞ እንዲታይ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት አድርጓል። ይህ ጦርነትም በዶ/ር አብይና በትግራይ ህዝብ መካከል የሚካሄድ ጦርነት ነዉ በሚል የራሱን ወንጀል ወደሌሎች ለማላከክ በብርቱ ሰርቷል፣ዛሬም ድረስ እየሰራ ነወሐ። አሳዛኙ ነገር አማራ ሁኖ ይሄንኑ አጀንዳ ተቀብሎ የሚያስተጋባ መኖሩ ነዉ።
ያም ሆነ ይህ አሜሪካ፣ትህነግና ተከፋዮቹ ከደቀኑብን ስጋት ለመላቀቅ ወሳኙ ጉዳይ ዉስጣዊ ሁኔታችን መሆኑ መታወቅ አለበት። የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም ደግሞ የአማራ ህዝብ ዉስጣዊ አንድነቱን ካጠናከረና አቅሙን ማስተባበር ከቻለ የነ አሜሪካ ዛቻም ሆነ የትህነግና ተከፋዮች ጊዚያዊ ድንፋታ የትም አይደርስም። እኛ ኢትዮጵያዊን አንድ እስከሆን ድረስ የዉጭ ወረራ በገጠመን ጊዜ ምን እንደምንሰራ እነ አሜሪካ የሚያዉቁት ድንቅ ታሪክ አለን። የአሜሪካ ጣልቃ ገብነት ሆነ የትህነግና ተከፋዮቹ ግብ የሚሳካዉ እኛ ኢትዮጵያዊያን በተለይም የአማራ ህዝብ አንድ መሆን ያቃተን እንደሆነ ብቻ ነዉ።
ስለዚህ አገራችንን ሆነ መንግስታችንን ከብተና ለመታደግ የሚያስችለን ቁልፍ ያለዉ በህዝባችን እጅ ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ እምቢ ካለ የአሜሪካ ዛቻ የትም አይደርስም። የቱርኩ ኤርዶጋን ከተቃጣበት ግልበጣ ተርፍ ዛሬ ላይ በምናየዉ ደረጃ የደረሰዉ አሜሪካ ስለፈለገች ሳይሆን፣የቱርክ ህዝብ በወሰደዉ ቁርጠኛ እርምጃ ነዉ። የቱርክ ህዝብ እንደዚህ አይነት ቁርጠኝነት ያሳየዉ ኤርዶጋንን በግለሰብ ደረጃ ስለወደደ አይደለም፤ ይልቁንስ ሰዉየዉ የሚመሩት መንግስት በዛን ወቅት ቢወድቅ በአገረ ቱርክ ሊከሰት የሚችለዉ ነገር ስላስፈራዉ ነበር። እዉነታዉ ይሄ ነዉ። ቱርካዊያን እንደዚህ አይነት ቁርጠኛ ዉሳኔ ላይ በመድረሳቸዉ አገራቸዉን ከምዕራብአዊያን ጫና በአንፃራዊነት አላቀዋታል።
ስለዚህ የኢትዮጵያ ህዝብ አገሩንና መንግስቱን ከብተና መታደግ አለበት ሲባል ነገሩን ከግለሰቦች ስልጣን ማራዘም ጋር ማያያዝ ጉዳት እንጅ ጥቅም የለዉም። የገጠመን ፈተና አገራዊ ዝቅ ሲል ደግሞ አማራዊ ሁኖ እያለ በጣም ወርዶና ነገሩን የግለሰብ ጉዳይ አድርጎ መመልከት አደገኛ ዉጤት ያስከትላል። ይሄንን የምለዉ አሁንም ነገሮችን ሳያገናዝቡ አቋም ለሚወስዱ ወንድም እህቶቸ እንጅ ሆን ብለዉ ለሚያጠፉትና ለትህነግ ተከፋዮች አይደለም። እነዚህማ ያለምንም ፍርሀት የአብይ መንግስት ወድቆ ህወሀት መር መንግስት እንዲመጣ በግልፅ እየሰሩ ስለሆነ ከነሱ ጋር ማዉራቱ ጉንጭ ማልፋት ነዉ።
በአጭሩ ወቅታዊዉ ምርጫችን በተለይም ከአማራ አንፃር ለአማራ የሚሻለዉ አሁን ያለዉ መንግስት ከነችግሩም ቢሆን እንዲቀጥል መታገል ነዉ? ወይንስ ይህ መንግስት ወድቆ ህወሀት መራሽ መንግስት እንደገና እንዲመጣ መፍቀድ ነዉ? በቃ ከነዚህ ምርጫወች ዉጭ በአሁኑ ወቅት ሌላ ምርጫ የለንም፤ ለጊዜዉ መሀል ላይ ሌላ መንገድ የለም፣ ከሁለቱ አንዱን መምረጥ ነዉ።
እኔ በበኩሌ ከነዚህ ምርጫወች መካከል ለአማራ ህዝብ የሚበጀዉ ከነችግሩም ቢሆን ይሄ መንግስት እንዲቀጥል መታገል ነዉ። ይሄንን የምለዉ ይህ ሳይሆን ቢቀር ሊከሰት የሚችለዉን ነገር ሳስበዉ ከወዲሁ ስለሚያስፈራኝ ነዉ። ብዙሀኑ የአማራ ህዝብም ይሄንኑ ሀሳቤን እንደሚጋራኝ ተሰፋየ ትልቅ ነዉ። አዉቃለሁ ለነ እንቶኔ ይሄ አቋሜ እንደ እሬት ይመራቸዋል። እኔ ደግሞ አስር ጊዜ ይምረራቸዉ እንጅ ለአገሬ በተለይም ለአማራ ህዝብ ሊጠቅመዉና ሊጎዳዉ የሚችለዉን ነገር መተንተንና መተንበይ አይከብደኝምና ለዚሁ ስል በዚሁ አቋሜ እገፋበታለሁ።
በመጨረሻም መላዉ የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም የአማራ ህዝብ አገርክንና መንግስትህን ከብተና ለመታደግ ከመቸዉም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ ዉሳኔ ላይ ድረስ። የአሜሪካን፣ትህነግና ተከፋዮቹን ኢትዮጵያን የማፍረስ ዛቻ እና ተግባራዊ እንቅስቃሰረ በተግባር አየር ላይ እናስቀረዉ።
መንግስትም ቢሆን የአብዛኛዉን ህዝብ ስሜት አዳምጦ ምላሽ መሰጠት ቢችል ጥሩ ነዉ። ህዝቡ ትህነግ ድል ተደርገቀ ማየት ናፍቆታል። ለዚህም ሲል ሁለንተናዉን ሰጥቷል/በመስጠትም ላይ ነዉ። በተለይም ህዝብ በአፀፋዉ ማጥቃት እንዲጀመር ከፍተኛ ጉጉት አለዉ። አዉቃለሁ ይገባኛልም፤መንግስት ሰራ ላይ እንደሆነ፣መሟላት ያለባቸዉ ቅድመ ሁኔታወችም በተገቢዉ መሟላት እንደሚገባቸዉ። ሁኖም በተቻለ መጠን ቀሪ ስራወችን በፍጥነት አጠናቆ ለህዝቡንና ዘማቹ ጥያቄ መልስ መስጫ ጊዜዉ አሁን ይመስለኛል።
አገራችንና መንግስታችንን ከብተና ለመታደግ ዛሬ ዉኑ ቁርጠኛ ዉሳኔ ላይ እንድረስ!!!

Comments are closed.