የህንዱ ድሮን አምራች ‹‹ቴክ ኤግል›› በኢትዮጵያ ውስጥ በድሮን እቃዎችን የማቅረብ አገልግሎት ሊጀምር እንደሆነ አስታወቀ፡፡

የህንዱ ድሮን አምራች ‹‹ቴክ ኤግል›› በኢትዮጵያ ውስጥ በድሮን እቃዎችን የማቅረብ አገልግሎት ሊጀምር እንደሆነ አስታወቀ፡፡

ይህ ድርጅት የህክምና ቁሳቁሶችንና ሌሎች አስፈላጊ ሸቀጦችን ከአንድ ቦታ ወደሌላ ቦታ በድሮን የማድረስ ስራ ለመስራት እንዲያስችለው ‹‹አዲስ መርካቶ›› ከተሰኘ የኢትዮጵያ ድርጅት ጋር ስምምነት መፈፀሙን ገልጿል፡፡ የቴክ ኤግል መስራችና ዋና ስራ አስፈፃሚ ቪክራም ሲንግ መና እንደተናገሩት አዲስ መርካቶ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚመለከታቸው አካላት ፈቃድ ለማግኘት በሂደት ላይ ነው፡፡

ሁለቱ ድርጅቶች በሚቀጥለው የፈረንጆች አመት የመጀመሪያ ወራት አገልግሎቱን ለመጀመር እንዳቀዱም አስረድተዋል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ እስካሁን ለድሮን ፈቃድ የሚሰጥ አካል የሌለ ሲሆን፣ በቅርቡ የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን የመጀመሪያውን የድሮን ህግ ረቂቅ ማውጣቱን መግለፁ ይታወቃል፡፡ ነገር ግን ይህ ረቂቅም ገና የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ሲሆን ለመፅደቅና ስራ ላይ ለመዋል ብዙ ሂደቶችን ማለፍ ይጠበቅበታል፡፡

Conso