ኮ/ል ልኡል ገብረዋህድ ብርሃኔ ከደቡብ ሱዳን ተላልፎ ተሰጥቶ በኢትዮጵያ መንግስት ቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ተረጋገጠ

(ዘ-ሐበሻ) በፌደራል ፖሊስ ከሚፈለጉት የሀገር መከለከያ ሚኒስቴር ሰብአዊ መረጃ ሃላፊ) ብ/ጄ መብራህቱ ወ/አረጋይ ፣ ኮ/ል ከበደ ገብረሚካኤል ፣ ኮ/ል ነጋሲ ስዩም በመሆን በሰሜን እዝ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ አመራሮችን ሲያሰልል እና ፕሮፋይላቸውን ለክልሉ የደህንነት ክንፍ ሲያቀብል የነበረው ኮ/ል ልዑል ገብረዋህድ ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፎ ተሰጥቶ በአሁኑ ወቅት በፌዴራል ፖሊስ ምርመራ ላይ እንደሚገኝ ዘ-ሐበሻ አረጋግጧል::

የሰሜን እዝ መረጃ ሃላፊ የነበረው እና አሁን በፍርድ ሂደት ላይ የሚገኘው በወላይታ ብሄራዊ ንቅናቄ ክንፍ አባልነት ጭምር የሚጠረጠው ብ/ጄ ኢናሶ ኢጃጆ ምክትል የነበረው ኮ/ል ልኡል ገብረዋህድ ብርሃኔ በሰላም አስከባሪነት በተሰማራበት ደቡብ ሱዳን ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ራሱ በዛዛው በደቡብ ሱዳን ሰላም ለማስከበር የተሰማሩትን የኢትዮጵያ ወታደሮች እርስ በእርሳቸው ለማፋጀት ከፍተኛ ሴራ ተቀብሎ ሲሰራ እጅ ከፍንጅ መያዙን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል::

ለረጅም አመታት የ20ኛ ክፍለጦር የመረጃ መኮንን ፣ የራማ እገላ ግንባር ወታደራዊ መረጃ መኮንን ሆኖ ያገለገለው ኮ/ል ልኡል ገብረዋህድ ብርሃኔ ከለውጡ በኋላ የሰሜን እዝ የሰብአዊ መረጃ መኮንን በመሆን ሲሰራ ነበር::

ከሚሰራቸው ሕገወጥ ድርጊቶች መካከልም ከሌሎች የትግራይ ክልል ባለስልጣናት ጋር በመመሳጠር ወደ ኢትዮጵያ ድንበር የሚገቡ ኤርትራውያንን ገንዘብ እየተቀበለ ከኬሎች ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን ወደ ሱዳን በማሻገር Human Trafficking ወንጀል ይሰራ ነበር:: በዚህም ባካበተው ሃብት ኮ/ል ልኡል በሽሬ ከተማ ዘመናዊ ቤት ገንብቷል::

“ከለውጡ በኋላ በመንግስት ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያደረበት መሆኑን “እኔ ወያኔ ነኝ” እስከ ማለት በደረሰ ሁኔታ ሲያንፀባርቅ የነበረ።” ሲሉ የሚቀርቡት ወታደሮች የሚናገሩለት ኮ/ል ልኡል ገብረዋህድ ብርሃኔ በአሁኑ ሰአት በፌደራል ፖሊስ ከሚፈለጉት ብ/ጄ መብራህቱ ወ/አረጋይ (የሀገር መከለከያ ሚኒስቴር ሰብአዊ መረጃ ሃላፊ) ፣ ኮ/ል ከበደ ገብረሚካኤል ፣ ኮ/ል ነጋሲ ስዩም በመሆን በሰሜን እዝ ውስጥ ያሉ ከፍተኛ አመራሮችን ሲያሰልል እና ፕሮፋይላቸውን ለክልሉ የደህንነት ክንፍ ሲያቀብል የነበረ ነው። ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት በደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ በሰላም ማስከበር ግዳጅ የነበረ ቢሆንም ከጥቃቱ በኋላም በሰላም አስከባሪው ሃይል መሀከል እኩይ የጥፋት ሴራን ለመከወን ሲንቀሳቀስ በመገኘቱ ለኢትዮጵያ መንግስት ተሰጥቶ በምርመራ ላይ ይገኛል። ሲሉ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ነግረዋል::

መረጃ/ስላላ ዘረፍ በብዙ ሴራ ተሳታፊ የነበረ ነው።