ትራፊው የሕወሃት ጁንታ የመቀሌን ሕዝብ ለአመጽ ለማነሳሳት መብራት ቆረጠ

የሃውዜን ጭፍጨፋ ልምድ ያለው ሕወሓት በትራፊ ተላላኪዎቹ አማካኝነት በመቀሌ ከተማ የተለያዩ ሳቦታጆችን እየፈጸመ እንደሆነ ተሰማ። ትናንት ለሶስት ቀናት የሚል የቤት ውስጥ አድማ እንዲጠራ ያደረገው ትራፊው ቡድን ዛሬ ደግሞ ሆን ተብሎ የመብራት መስመር ቆርጧል።

ከዚህ ቀደም ጦርነቱ በተጀመረ ግዜ ሕወሃት የስልክ እና የመብራት መስመሮችን ቆራርጦ ህዝቡን በጨለማ ውስጥ ከጣለው በኋላ ውጫ ባሉ ተላላኪዎቹ አማካኝነት ደግሞ “ስልክም መብራትም የትግራይ ሕዝብ አጣ” በሚል በሰላማዊ ሰልፍ ሲጮህ ይስተዋላል።

የግ ዕዝ ሚድያ አዘጋጅ አማንሚካኤል መስፍን በጉዳዩ ላይ እንዲህ ይላል።
መቐለ ላይ ዛሬ ጥዋት መብራት ጠፍታለች አሉኝ እና
“ የህወሓት ታጣቂ ” ትላንት በጥሰውታል ብለው በኩራት ነገሩኝ።
እኔ ደሞ እንበል እና መብራት የጁንታው ታጣቂ መብራቱ አጠፋው እንል እንዴት ይሄ በኩራት ያስነግራል ? ማንስ ነው የሚጎዳው? አልኳቸው። ይህ ፀያፍ ስራ ተሰርቶ ከሆነ ህዝብ ሊኮንነው ይገባል። መብራት በማጥፋት የመንግስት ባለስልጣን አይጎዳም የሚጎዳው ህዝቡ ነው።
የንግድ ሱቅ መዝጋትም ለራሱ ለነጋዴው እና ለትግራይ ህዝብ ነው የሚጎዳው እንጂ ሌላ ፋይዳ የለውም።
ትምህርት ይጀመራል በመቐለ ተብሎም ወላጆች ልጆች አንልክም ብለዋል። ይሄም የሚጎዳው የትግራይ ህዝብ ነው። ህዝባችን ትምህርት ቤት ክፈቱልን ማለት ነው ሲገባው ጭራሽ አንልክም ማለቱ ጉዳቱ ለራሱ ለህብረተሰቡ ነው።
አሁን ከላይ የጠቀስኳቸው አድማዎች ለራሱ ለህዝቡ እንጂ ለመንግስት ሆነ ለመንግስት ሹመኛ ምንም ጉዳት የለውም።” ይላል።

በሌላ በኩል አንድ የመከላከያ ሰራዊት አባል በማህበራዊ ገጻቸው ባሰራጩት መረጃ “ትግራይ ሶማሊያ ሆናለች።
አሁንም ህዝቡ መሃል የመሸጉ ርዝራዦችን ለማፅዳት የስምሪት ለውጥ ማድረግ ያስፈልጋል።
ከሰሜን እዝ ጥቃት እና እገታ የተረፉትን ሁሉንም ወታደሮች መልሶ ትግራይ ላይ ማሰማራት ተገቢ ይሆናል። ወታደሮቹም በተደጋጋሚ ለመንግስት እየጠየቁ ያሉት ይህንን ነው። “አስታጥቁን! ወደ ነበርንበት ቦታ መልሱን!”
ሰሜን እዝ ላይ የነበሩ ወታደሮች የክልሉን መልክዓ ምድር እና ጓዳ ጎድጋዳ ከማወቅም በላይ በጥቅምት 24ቱ የክህደት ጥቃት የት ላይ ማን ምን እንዳደረጋቸው ከእነሱ በላይ የሚያውቅ የለም። በተለይ ከውስጥ ሆነው በክህደት የገደሏቸውን እና ያስገደሏቸውን አሁን ደሞ እንደ ሰላማዊ ሰው ከህዝቡ ጋር ተመሳስለው በመንቀሳቀስ ንፁሃን ዜጋን የብልፅግና ደጋፊ ነህ ገለመለ እያሉ እያሰቃዩና እየገደሉ የሚገኙትን ነጥሎ ለማፅዳት ሁነኛ መፍትሄ ነው።
ከጥቃት የተረፉት የሰሜን እዝ ወታደሮች በሙሉ ከ20 አመት በላይ ወዳገለገሉበት ትግራይ ክልል ዳግም ተሰማርተው ወንበዴዎችን የማጥራት ዘመቻውን እንዲያሳልጡ እድል ሊሰጣቸው ይገባል። በተለይ 4ኛ ሜካናይዝድ ክፍለጦር የነበሩ አባላት ሳይውል ሳያድር የትግራይ ስምሪትን ወስደው ቢንቀሳቀሱ ርዝራዡን እስከ ቅሪቱ ለወሬ ነጋሪ ሳያስቀሩ አፈር ድሜ እንደሚያበሉት አልጠራጠርም።”