በትግራይ ም ዕራብ ሽሬ አካባቢ ተኩስ የከፈተው የሕወሓት ኃይል በ20 ደቂቃ ውስጥ ተደመሰሰ

ለረዥም ጊዜ በተከዜ በረሃ መሽጎ እጅ አልሰጥም ያለው የሕውሓት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ከተደመሰሰ በኋላ  በትግራይ ጦርነት የሚባል ነገር የለም ሲሉ አንድ የመከላከያ ምንጭ ለዘ-ሐበሻ ገለጹ። የመከላከያው ምንጭ ሕወሓት ሲተመንበት የነበረው የተከዜው በረሃ ጦር ከተወገደበት በኋላ አሁን በየአካባቢው ተበታትኖ የቀረ ሰራዊት ነው ያለው ብለዋል።

Shire Map

በየስፍራው ተበታትኖ ያለው የሕወሓት ኃይል ጦርነት የማድረግ አቅም የለም ግን ለ10 እና ለ20 ደቂቃ ለማይበልጥ ጊዘ ውጊያ ከፍቶ ይደመሰሳል ብለዋል።

በሽሬ አካባቢ የመሸገው የሕወሃት ጦር በመከላከያው ላይ ውጊያ ከፍቶ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በ20 ደቂቃ ውስጥ ደምስሶታል። በሌሎች አካባቢዎችም የሕወሃት የጦር አባላት እና አንዳንድ አመራሮች እጅ እየሰጡ እንደሆነ የሚናገሩት እኚሁ ምንጭ አዲስ አበባ የተቀመጠው የመከላከያ ኃይል የሚዲያ አመራሮች ነገሩን ለሕዝብ እንዳይገለጽ የሚያፍኑበት ልግመኝነት እርሳቸውንም እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ለምሳሌም ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄ መሀመድ ተሰማ  ዛሬ በሰሜን መከላከያው እያደረገው ያለውን ተጋድሎ ከመግለጽ ይልቅ ራሳቸው የተሳተፉበትን የሽኝት መርሃ ግብር በመከላከያው ሚዲያ እንዲዘገብ አድትገዋል። ሀገርን ወክለው ወደ  ጁባ የሚሄዱ የሠራዊት አባላት የምንም ዓይነት ልዩነት ሳይኖር ለቆሙለት አላማ በፅናት መሠለፍ እንዳለባቸው መናገራቸውን የሚገልጽ ዜና ነው ያስነገሩት።

ወደ ደቡብ ሱዳን ጁባ የሚያቀኑ የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻላቃ አባላት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት  እንደተሰጣቸው፤  ወደ ጁባ ለሰላም ማስከበር የሚዘምቱ የሠራዊት አባላትም በሄዱበት ሀሉ ስኬታማ ሥራ በመሥራት የሀገራቸውን ሥም ለማስጠራት  መዘጋጀታቸውን መናገራቸውን የሚገልጽ ዜና ሲያስግሩ ታይተዋል።

በተከዜ በርሃ ከተደመሰሰሱ የሕወሓት ሰራዊት አባላት ውስጥ እነማን እንደተደመሰሱ ለማወቅ እስካሁን እንዳልተቻለም ሰምተናል። የአካባቢው መልከአ ምድር እጅግ አስቸጋሪ በመሆኑ እንዲሁም በአውሬ አስከሬናቸው የተባለ እንዳለና አካባቢውም እጅግ ስለሚሸት የመለየቱን ስራ አስቸጋሪ እንዳደረገው እኚሁ ምንጭ ገልጸዋል።