በመቀሌ ከተማ ሱቆች አድማ አድርገው ዋሉ – የሕወሓት ትራፊዎች የተዘጉትን ሱቆች እየዘረፉ ነው

ትግራይ ከተረጋጋች እረሳለሁ ብሎ የሚያስበው የሕወሓት ርዝራዥ ቡድን ትግራይ እንዳትረጋጋ የማይፈነቅለው ድንጋይ ይለም ይላሉ አስተያየት ሰጪዎች። እርዳታ ሕዝብ ጋር እንዳይደርስ ሆን ብሎ በአንዳንድ አካባቢዎች ተበታትነው በሚገኙ ወታደሮቹ አማካኝነት ውጊያ የሚከፍተው ሕወሓት፤  ይህን  እያስተግጎለ፤ በሌላ በኩል ደግሞ እርዳታ ለሕዝቡ አልደረሰም በማለት ያስጮሃል። 

በውጭ ያሉ የሕወሃት ሚዲያዎች በመቀሌ ከተማ ዛሬ የአመጽ ጥሪ አቅርበው የነበረ ሲሆን በዚህም መሰረት በስጋት ውስጥ ያሉ የከተማዋ ነጋዴዎች ንግድ ቤቶቻቸውን ዘግተው ውለዋል።  በከተማዋ የተሰገሰጉት  ሕወሃት ሕዝቡን የሚያማርሩ ሌቦችን በማስማራት ዛሬ በመቀለ ከተማ የተዘጉትን ሱቆች በሌላ በኩል ሲያዘርፍ መዋሉን ከስፍራው የመጡ መረጃዎች አመልክተዋል።

ውጭ ካሉት ሚዲያዎች በተጨማሪም በከተማዋ ለሶስት ቀናት ሕዝቡ በቱ እንዲቀመጥ የሚጠይቅ ወረቀት በድብቅ ሲበተን ነበር።     ወረቀቱም ” ለሶስት ተከታታይ ቀናት ከቤት ባለመውጣት ህዝባዊ እምቢተኛነታችሁን ግለፁ ” የሚል ነበር።

በመቀሌ መከላከያ ሰራዊቱና ፊዴራል ፖሊስ በወሰዱት እርምጃ የስርቆት ወንጀሎች ጋብ ብለው የነበረ ሲሆን ዛሬ የተጠራውን አመጽ ተከትሎ ግን ንግድ ቤቶቻቸውን የዘጉት ሆን ተብለው ነው የተዘረፉት ተብሏል። ይህም ሕዝቡ ሕወሓትን እንዲናፍቅ እና እንዳይረጋጋ ለማድረግ የሚደረግ ሴራ ነው ተብሏል። 

ይህ በ እንዲህ እንዳለ የኤርትራ አየር ሃይል ወታደራዊ ድሮኖችን ለመጠቀም የሚያስችለውን ስራ እየስራ ነው ሲል ኤርትራን ፕሬስ ዘገበ።

የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የታጠቁ ድሮኖች በኤርትራ አሰብ ወደብ ላይ ቤዝ እንዳላት ዘገባው አክሎ ገልጿል:: 

የክንፋቸው ስፋት 20 ሜትር የሆኑ ዊንግ ሎንግ የተሰኙ ቻይና ሰራሽ ድሮኖች ሲሆኑ እነዚህ ድሮኖች ቦምብ የሚጥሉ እና ሚሳኤሎችን የሚመቱ ናቸው ሲል ኤሪትሪያን ፕሪስ አስታውቋል። ደቡብ አፍሪካ : አልጀሪያ፣ ግብፅ : ኢትዮጵያ፣ ናይጄሪያ እና ኤሪትሪያ በአፍሪካ የጦር ድሮን ያላቸው ሃገራት ናቸው።

መቀሌ ከሕወሓት ጁንታ ነጻ ከወጣች 71ኛ ቀኗ ሲሆን በነዚህ 71 ቀናት ከተማዋ እንዳትረጋጋ ሕወሓት የማይፈነቅለው ድንጋይ አልነበረም።