ተቆርጦ የቀረ የሕወሓት ጦር በሁለት አካባቢዎች መደምሰሱ ተሰማ

ከቆላ ተንቤን በረሃ ከትሞ የነበረው የሕወሓት ጦር በ4 ቀን ጦርነት ከተደመሰሰ በኋላ አሁን ደግሞ በሌሎች የትግራይ ገጠር አካባቢዎች ተቆራጠው የቀሩትን የሕወሓት ጦር አባላት የማሳደዱና የመደምሰሱ ሥራ እንደቀጠለ መሆኑን የዘ-ሐበሻ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል።

ከአክሱም ወደ ሽሬ በሚያስኬደው መንገድ አካባቢ በምትገኝ አፍጋህጋ በተባለች አካባቢ ተራራ ውስጥ ከትሞ የከረመው የሕወሓት ጦር በአካባቢው ነዋሪ ላይ ዘረፋ እና አስገድዶ መድፈር ሲፈጽም የቆየ ሲሆን በትናንትናው ዕለት ደግሞ ረሃብተኛው የሕወሃት ሰራዊት ምግብ ፍለጋ በስፍራው የነበረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ ተኩስ ከፍቶ ነበር። 

የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊትም የአፍጋህጋ ተራራን በማስለቀቅ በስፍራው ተራርፎ የተቀመጠውን የሕወሃት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ደምስ ሶታል። በረሃብ የተጎዱ የሕወሃት ሰራዊት አባላትም መካከልም የተወሰኑት እጃቸውን ለኢትዮጵያ መንግስት መስጠታቸውን ምንጩ ገልጸዋል።

በለላ በኩልም በራያ ተራሮች ላይ መሽጎ የቆየው ረሃብተኛው የሕወሓት ሰራዊት በምግብ እጦት ሲሰቃይ ቆይቶ በመጨረሻም ምግብ ፍለጋ ያለ የለለ ኃይሉን ተጠቅሞ በኢትዮጵያ መካለካያ ሰራዊት ላይ ድንገት ጥቃት ፈጽሞ አንድ የኢትዮጵያ መከአከያ ሰራዊት አባል በክብር ከተሰዋ በኋላ ተራራውን ለማጽዳት የተንቀሳቀሰው ሰራዊቱም በስፍራው ተደብቀው የነበሩ የሕወሓት አመራሮችን ጭምር መደምሰሱ ተገልጹዋል። የኢትዮጵያው ወታደር ቀብርም በክብር የተፈጸመ ሲሆን በአካባቢው ሙሉ በሙሉ ተቆርጦ የቀረው የሕወሃት ሰራዊት መደምሰሱን እና የሞቱትን ማንነት የማጣራት ሥራ እየተሰራ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።