“..ባለመዶሻ፤ ያየው ችግር ሁሉ ሚስማር ይመስለዋል…”

ማርክ ትዌይን ሲያሾፍ “..ባለመዶሻ፤ ያየው ችግር ሁሉ ሚስማር ይመስለዋል…” ይላል። የሕወሃት ደጋፊዎችም ኢትዮጵያን በውሸት የሚያሸንፉ ይመስል ሃሰተኛ መረጃ በመልቀቅ የሃገሪቱን ስም ሊያጠለሹ ይሞክራሉ።  ባለመዶሻው ችግር የሚለው ሁሉ ሚስማር እንደሚመስለው ሁሉ ጥቅም የቀረባቸው የሕወሓት ሰዎችም ሽንፈታቸውን የሚያስታግሱት ውሸት በማውራት፤ በውሸት ሃገሪቱን እና ለሃገሪቱ ደሙን እየከፈለ ባለው መከላከያ ሰራዊታችንን በመወንጀል ነው። 

እንዲህ ያለውን ሃሰተኛ መረጃ ተራው ሰው ቢያሰራጨው ምንም ላይመስል ይችላል። የኢትዮጵያ ሕዝብ በሥራቸው አክብሮ ላይ የሰቀላቸው ሰዎች ሲዋሹና የሃገርን ክብርና መልካም ገጽታ ሲያጠፉ ግን ንቆ ማለፍ የድርጊታቸው ተባባሪ መሆን ነው።

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ካላት ምርጥ ከሚባሉ አርቲስቶች መካከል ሰላም ተስፋዬ በግንባር ቀደምትነት የምትጠቀስ ናት።

ሰላም ኢትዮጵያዊት የፊልም ተዋናይት እና ሞዴል በ1986 ዓ.ም ሀረር ተወልዳ ሕወሓት በግፍ ወደ ወሰደው ሑመራ በመሄድ ከ እናቷ ጋር አብራ ኖራለች። ሰላም በሃረር ተወልዳ በለሎች የኢትዮጵያ ከተምች በ እናቷ ስራ ምክንያት እየተዟዟረች ብትኖርም ለረዥም ጊዜ ያደገችባትና የተማረችባት ሁመራ ከተማ ትዝታ ግን ከልቧ እንደማይጠፋ ትናገራለች። ስላም የ17 ዓመት ልጅ እያለች ሁመራን ለቃ አዲስ አበባ በመግባት ከልጅነቷ ጀምሮ የምትመኘውን ተዋናይ የመሆን ሕልሟን ለማሳካት የቻለች አርቲስት ናት።

 በ2010 ዓ.ም ከፊልም ኤዲተሩ አቶ አማኑኤል ተስፋየ ጋር ትዳር መስርታ የአንድ ልጅ እናት የሆነችው ሰላም በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ እንድትወደድ ባደረጓት  “ቢሆንስ” ፣ “ፍቅር በይሉንታ” ፣ “ቫላንታይን” ፣ “ሶስት ማዓዘን” ፣”ህይወት በደረጃ” ፣ “እሷን ብዬ” ፣ “አልማዜ” ፣ “ሚስ ቨርጅን” ፣ “በጭስ ተደብቄ” ፣ “ፍሪደም” ፣ “ልክ ነኝ” ፣ “ያበደች የአራዳ ልጅ” ፣ “የተከለከለ” ፊልሞች ላይ በብቃት ተውናለች።

በትግራይ የቁንጅንና ውድድር በአንድ ወቅት  ሁለተኛ የወጣቸው ሰላም ፣ “ያበደች የአራዳ ልጅ” ፊልም በ9ኛው አዲስ ሙውዚክ አዋርድ ምርጥ ተዋናይት አስብሏታል። በፊልሙ አለምም ሆነ በምታከናውናቸው በጎ ተግባራት የተለያዩ ሽልማቶችን እና ምስጋናዎችንም ከሕዝብ አግኝታለች።

“የጨው ክምር ሲፈርስ ሞኝ ያለቅስ፤ ብልህ ይልስ” እንዲሉ ሕወሓት ከወደቀ በኋላ የሕወሓት ተጠቃሚዎች ሲያለቅሱ ኢትዮጵያን ወዳድ የትግራይ ተወላጆች ህወሃትን ረስተው ህዝባቸውን ለመርዳትና ሃገራዊ አንድነቱን ለማጠናከር እየሰሩ ነው።

አርቲስት ሰላም ተስፋዬ ሐረር ተወልዳ በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች ኖራ በሑመራ እንደማደጓ ብዙ ነገሮችን ስላየች ኢትዮጵያዊ አብሮነትን እና ሕዝብን እንደምታስቀድም ማንም አይጠራጠርም። ሆኖም ግን ሕወሓት ከተወገደ በኋላ በተለይም በኢንስቴግራም ገጿ ላይ የምታንጸባርቃቸው ሃሳቦች ለርሷ ያለንን ግምት ቢያወርደው አይደንቅም።

በተለይ በዛሬው ዕለት በኢስታግራም ገጿ የለጠፈችው ሃሰተኛ ፎቶ ሕዝብን ከማሳሳቱም በላይ ብዙ ተከታዩቿ በኢትዮጵያ ላይ የተንሻፈፈ አቋም እንዲኖራቸው የሚያደርግ ነው።

ሰላም ኢንስቴግራም ገጿ ላይ 590 ሺህ ተከታዮች አሏት። ይህ በጣም ትልቅ ቁጥር ነው። ከኢንስተግራም ብዙ ተከታይ ካላቸው አርቲስቶች መካከልም አንዷ ናት። ስለዚህም ለምትለጥፋቸው ነገሮች፤ ስለምታሰራጨው መረጃ እውነተናነት በጣም ሃላፊነት ሊሰማትይገባል። እንኳንም ከግማሽ ሚሊዮን በላይተከታይ ያለው ይቅር እና ትንሽዬ የማህበራዊ ሚዲያ ተከታይ ያለው ሰው ከቅርብ ሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞቱ ብሎ ባሰራጨው ሃሰተኛ መርጃ ስንት ውዥንብር እንደፈጠረ የምናውቀው ነው። ጃዋር መሐመድ በፌስቡክ ገጹ በጻፈት ሁለት መስመር ጽሁፍ ስንት ከሁለት መቶ በላይ ንጹሃን ዜጎች ዘራቸው እና ሃይማኖታቸው እየተመረጠ እንደተገደሉ የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው።

ሰላም ተስፋዬ 590 ሺህ ተከታይ ባለው ኢኒስተግራም ገጿ ላይ ትግራይ ክልል ውስጥ ቤተክርስቲያን በጦርነቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አፈረሰ እየተባለ እየተሰራጨ ያለውን ሃሰተኛ ፎቶ ግራፍ ልቧ እንደተሰበረ አድርጋ ለጥፋ ብዙ ሰዎችን አሳስታልች። ፎቶው በዲጂታል ወያኔ የተለቀቀ ኤርትራ ሰንአፌ ከተማ ውስጥ ከዓመታት በፊት የተፈጸመን ልክ ትግራይ ውስጥ አሁን እንደተፈጸመ በማስመስል የተለቀቀ ነው። በዚህም የዓለም አቀፍ ሚዲያዎችን ለማሳሳት እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ላይ መጥፎ ስም ለማሰጠት የተሰራ ሴራ ነው።

ሰላምም ይህንን የዲጂታል ወያኔ ፎቶ ግራፍ ለጥፋ ብዙ ሰዎችን ካሳሳተች በኋላ በርካታ ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን በማጋለጣቸውና ፎቶው ትግራይ ውስጥ ሳይሆን ኤርትራ ውስጥ የተፈጸመ መሆኑን ስትረዳ ከገጿ ላይ ከሰዓታት በኋላ ብታጠፋውም ይቅርታ ግን አልጠየቅችም። ይህን ሃሰተኛ ፎቶ በማሰራጨት 690 ሺህ ተከታዮቿን በማሳሳቷ ይቅርታ ሳትል ፎቶውን አጥፍታ ዝም ማለቱ ከአፈርኩ አይመልሰኝ  የሚያስብል ነው።

ማርክ ትዌይ “..ባለመዶሻ፤ ያየው ችግር ሁሉ ሚስማር ይመስለዋል…” እንዳለው ሁሉ እነሰላምም ሆነ የህወሃት ደጋፊዎች ሊረዱት የሚገባው ለሕወሓት ሽንፈት ማካካሻ መፍትሄው ሃሰተኛ መረጃ ማሰራጨት አለመሆኑን ሊገነዘቡ ይገባል። አይ ካሉና በውሸት መረጃው ከቀጠሉበት እየተከታተሉ ማጋለጡ እና ካስቀመጥናቸው የክብር ስፍራ ማወረዱ ደግሞ የኛ የኢትዮጵያውያን ሥራ ይሆናል።

በመጨረሻም! ሰላም ለትግራይ ሕዝብ ማዘኗ መጨነቋ እና እርዳታ ለማሰባሰብ መሞከሯ የሚደገፍና የሜበረታታ ተግባር ነው። ምንም እንኳ “አስቤዛ ለትግራይ” በሚል የጀመረችው እንቅስቃሴ ከሕወሓት ደጋፊዎች ጋር በተከሰተ የ እርስ በ እርስ መጠላለፍ ቢቆምም እውነት ለትግራይ ህዝብ እርዳታ ማድረስ ከፈለገች እነታማኝ እና ሌሎች የትግራይ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ልጆች የጀመሩትን የእርዳታ ማሰባሰብ ልትቀላቀልና ልታግዝ ትችላለች።

ሰላምዬ! “የተረገመችን እግር በቅሎ ነስቶ ጫማ ያሳጣታል” እንዲሉ መሰረትሽ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ ሕወሃት አይደለምና ከመሠረትሽ የኢትዮጵያ ሕዝብ  ጋር አትጣይ፤ ለሁልጊዜ መሰረት ይሆንሻልና።