የሕወሓት ሰዎች በቀይ መስቀል መኪና የጦር መሳሪያ እያደረሱ መሆኑ ተደረሰበት | አንድ ጥይት የያዘች የኢትዮጵያ ቀይመስቀል የመቀሌ ጽህፈት ቤት አምቡላንስ ተያዘች

አንድ ጥይት የያዘች የኢትዮጵያ ቀይመስቀል የመቀሌ ጽህፈት ቤት አምቡላንስ ተያዘች

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በየቦታው ተቆራርጠው የቀሩትን እና በገጠር እህል ለማድረስ የሚሄዱ ሰላማዊ የመሃል ሃገር ሰዎች የሆኑ ሹፌሮችን እየገደሉ እህል እየዘረፉ ለሚገኙት አንዳንድ የሕወሓት ታጣቂዎች የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የመቀሌ ቅርንጫፍ አምቡላንሶችን በመጠቀም ሎጂስቲክ ሲላክላቸው መቆየቱ ተደረሰበት።

Ethiopia Red Cross Society Ambulance

በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ የተሸሸጉ የሕወሓት ተላላኪዎች በኔትወርክ በመያያዘ ለጁንታው አባላት የጦር መሳሪያዎችን፣ የህክምና መሳሪያዎችን እና ምግቦችን በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የመቀሌ ቅርንጫፍ አምቡላንሶችን በመጠቀም እያደረሱ ቆይተዋል።

ሆኖም የካቲት 25 በደረሰ አስቸኳይ ጥቆማ አንድ የቀይ መስቀል አምቡላስ ሙሉ ጥይት ጭና ለልጁንታው ለማድረስ ስትንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር ውሏል። በወቅቱ ሹፌሩና ተባባሪዎቹ ለማምለጥ ሲሞክት እንደተያዙ የሚናገሩት የዘ-ሐበሻ ምንጮች ምርመራ እየተደረገበት መሆኑ ገልጸውልናል።

በአሁኑ ሰዓት በመቀሌ የሚገኙ የቀይ መስቀል አምቡላንሶች ሕዝብን ለማገልገል በስፍራቸው የሌሉ መሆኑን የሚገልጹት ምንጮቹ አብዛኞቹ ለጁንታዉ አገልግሎት እየሰጡ በመሆኑ መከላከያውም ሆነ በስፍራው ያለ የፌዴራል ፖሊስ ይህን ተገንዝቦ በቀይ መስቀል መኪናዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በሽተኛ የያዙ በማስመስል፤ ሳይረን እያበሩና እያስጮኹ በማለፍ ለጁንታው ሎጅስቲክ በማቅረብ ላይ ናቸው አምቡላንሶቹ ብለዋል።

በመቀሌ ከሚገኙ የቀይ መስቀል ሰራተኞች አብዛኞቹ በስራ ቦታቸዉ የሌሉ መሆኑን የሚገልጹት ምንጮቹ ጂንታዉን ሳይቀላቀሉ እንደማይቀሩ እየተነገረ ነው።

የተለያዩ ክልሎች ከፌዴራል መንግስት በተሰጣቸው አቅጣጫ መሰረት ለትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ አምቡላንሶችን፣ የገንዘብ እና የእህል እርዳታ እያደረጉ መሆኑ መገለጹ አይዘነጋም።