ጌታቸው አሰፋን በተመለከተ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጌታቸው አሰፋን በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆነ ተመልክተናል። ብዙ የዘ-ሐበሻ ቤተሰቦችም መረጃውን እንድናጣራ ጠይቀውናል። ዘ-ሐበሻ ስለጌታቸው አሰፋ መገደል ከምንጮቹ እስካሁን ድረስ ለማረጋገጥ አልቻለም። በአማራ እና ትግራይ ክልል አቅጣጫ በሰቆጣ አቅጣጫ በርካታ የሕወሃት ሰዎች እንደተደመሰሱ መረጃው ዘ-ሀበሻ እጅ ያለ ሲሆን በጥቅሉ ጌታቸው ተገደለ የሚለውን ምንጮች ሊያረጋግጡልን አልቻሉም እንዳረጋገጡልን ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን። ይጠብቁን፡:


ባለፈው ቅዳሜ ባሰራጨነው 3 መረጃዎች ላይ በዋግ አካባቢ ጌታቸው አሰፋ እና ጀነራል ታደሰ ወረደ በኮንቮይ ታጅበው መታየታቸው እና መከላከያው ሲመጣባቸው እንደሸሹ፤ ጌታቸው አሰፋም ቆስሎ እያነከሰ እንደሚሄድ ከተማረኩ የሕወሓት ወታደሮች መሰማቱን መዘገባችን ይታወሳል።