“በብልቃጥ ውስጥ ያለ ስኳር ስኳር እንጂ ስኳሮች አይባልም” – ታማኝ በየነ

ውድ የዘ-ሐበሻ ቤተሰቦች በዛሬው ዕለት ይዘንላችሁ የመጣነው አንድ ታሪካዊ ቪድዮ ነው። ታሪካዊ ቪድዮውን ዛሬ ለምን ለማቅረብ አስፈልገ? ለምትሉ እንግዲህ ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በአዲስ አበባ የአማራ ልማት ማህበር ለሚያሰራው የአማራ ባህል ማዕከል ማስጀመሪያ ላይ ባደረጉት ንግግር ላይ እኛ ሕዝብ እንጂ ሕዝቦች አይደለንም ሲሉ የተናገሯትን ንግግር አይተን ታማኝ በየነም ከሃገር ሳይወጣ በ1988 በኢትዮጵያ አቆጣጠ ገደማ በማምህራን ማህበር ምስረታ 47ኛው ዓመት በዓል ላይ የተናገረውን ለማስታወስ ነው። ታማኝ “በብልቃጥ ውስጥ ያለ ስኳር ስኳር እንጂ ስኳሮች አይባልም” ይላል።
እስኪ ንግግሩን ያድምጡት – እና አስተያየት ስጡበት።