www.zehabeshanews.com

ሕወሓት ሁለት ጊዜ ደመሰስኳቸው ሲል መረጃ ያሰራጨባቸው ሜጄር ጀነራል ዘውዱ በላይ ዛሬ በአዲስ አበባ በቴሌቭዥን ታየ

Views: 74

ሕወሓት ለሁለት ጊዜያት ያህል ደመሰስኳቸው ሲል መረጃ የለቀቀባቸው ሜጄር ጀነራል ዘውዱ በላይ ዛሬ በአዲስ አበባ ማዕከላዊ ዕዝ ሲችዌሽን ሩም ሆነው የነገውን ምርጫ ተከትሎ ሪፖርት ሲያዳምጡ በቴሌቭዥን ታይተዋል።

ሕወሓት ላለፉት 3 ቀናት ዘመቻ አሉላ አባነጋ በሚል ውጊያ ከፍቻለው ካለ በኋላ ስም እየጠራና እና ፎቶ እየለጠፈ ጄነራሎችን ደመሰስኩ፤ ማረኩኝ እያለ እያስወራ ሲሆን ከነዚህም መካከል የምስራቅ ዕዝ አዛዡ ሜጀር ጀነራል ዘውዱ በላይ ናቸው። ዘውዱ በላይን ከዚህ ቀደምም ደምሰሻቸዋለሁ ሲል መግለጫ የሰጠው ህወሓት አሁንም ለሁለተኛ ጊዜ ይህን እያስወራ ቢሆንም ጀነራሉ ዛሬ በቴሌቭዥን መስኮት ታይተዋል።

ሕወሓትን በራያ ግንባር በኩል ተሸንፎ እንዲባረር ያደረጉት ጀነራሉ ህወሐት ለዓመታት ያዋጋኛል ብሎ የቆፈረውን ምሽግ ጀግናው ሠራዊታችን በመሰባበር ከጁንታው ብቻ ሳይሆን አስቸጋሪ ከሆነ መልክአ ምድር ጋር ተፋልሞ ድል ኧንዲያደርግ በማድረጋቸው እጅጉን አምርሮ ከሚጠላቸው የኢትዮጵያ ጦር አዛዦች መካከል አንዱ ናቸው።

ከጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ አይበገሬው የሚል ስያሜ የተሠጣቸው ሜጀር ጄኔራሉ በወቅቱ ሕወሓትን ድል ሲያደርጉ በሰጡት መገልቻ ÷ “በህግ አልዳኝ ብሎ ግጭት የመረጠውን ጁንታ ሠራዊታችን በአጭር ግዜ ውስጥ ከሀገር ወዳዱ የትግራይ ህዝብ በመነጠል ሙሉ በሙሉ ከስራ ውጭ አድርጎታል” ብለዋል ።
ሜጀር ጄኔራል ዘውዱ በላይ ሠራዊቱ “ ከቢሶ በር – ጨርጨር ፣ መኾኒ ፣ አዲቀይህ ፣ አዲመስኖ እና ሌሎች ቦታዎች ላይ ለዓመታት ያዋጋኛል ብሎ የቆፈረውን ምሽግ ጀግናው ሠራዊታችን በመበጣጠስ ከጁንታው ብቻ ሳይሆን በጣም አስቸጋሪ ከሆነ መልክአ ምድር ጋር ተፋልሞ ድል አድርጓል” ብለዋል።
ህዝብና መንግስት ለቀጣይም ቢሆን በየትኛውም ግዜና ቦታ ለሚሠጠን ግዳጅ ደከመኝ ፣ ሠለቸኝ የማይል ብቃት ያለው ሰራዊት እንዳለን በነበሩት የህግ ማስከበር ዘመቻዎች ተረጋግጧል” ሲሉም መግለጻቸውን ኢዜአ ከመከላከያ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያሳያል

Comments: 0

Your email address will not be published. Required fields are marked with *