የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ጊዜያዊ የቆጠራ ውጤት በየምርጫ ጣቢያው እየተለጠፈ ነው

የ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ጊዜያዊ የቆጠራ ውጤት በየምርጫ ጣቢያው እየተለጠፈ ነው። ምርጫ ቦርድ ውጤቱን ይፋ ማድረግ የሚጠበቅበት ቢሆንም በጊዜያዊ ውጤት ግን የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ከፍ ያለ ውጤት እያገኘ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ባህርዳር ጊዜያዊ የቀድሞው የአብን ሊቀ-መንበር ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር) እየመሩ መሆኑ ተገልጿል። በጎንደር ብልጽግና ፓርቲ ተወካዮች በተለያዩ ምርጫ ጣቢያዎች እየመሩ መሆኑ ተገልጿል።

ከላይ ጋይንት! ምርጫ ክልል1 ለክልል ምክር ቤት ብልጽግናን ወክሎ ተወዳዳሪ የሆነው ፍቃዴ ዳምጤ በ68 እየመራ ነው። የገቢዎች ሚኒስትር የሆኑት አቶ ላቀ አያሌው በዳሞ ለብልፅግና በመወዳደር ለክልል ም/ቤት አባል ተወዳድረው እየመሩ መሆኑን ጊዜያዊ ውጤቶች ያመለክታሉ።

በቋሪት ምርጫ ክልል ለፌደራል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተወዳደረው የአብኑ ክርስቲያን ታደለ እየመራ ነው ተብሏል። እንዲሁም የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ለክልል ም/ቤት ብልጽግናን በተወዳደረሩበት ፎገራ 1 ምርጫ ክልል እየመሩ ነው።

ሰሜን ሸዋ ላይ ብልጽግናን ወክለው የተወዳደሩት ዶክተር ደረጄ ተክለማርያም እና ወ/ሮ ገነት ቤተ እየመሩ ይገኛሉ።

በቻግኒ የተወዳደሩት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን እየመሩ መሆኑም ከተለጠፉ ጊዜያዊ ውጤቶች ተመልክተናል።

የአማራ ክልል ር ዕሰ መስተዳድር አገኘው ተሻገር ለክልል ምክር ቤት ጎንደር ላይ ተወዳድረው እየመሩ ነው።

በወሎ አካብቢ ብልጽግና ፓርቲ ተወካዮች እየመሩ መሆኑን ጊዜዊ ውጤቶች ያሳያሉ።

በአዲስ አበባም የተለያዩ አካባቢዎች ከወጡ መረጃዎች ለመረዳት እንደሚቻለው በአብዛኛው ብልጽግና ፓርቲ እየመራ ይገኛል። በግል የተወዳደሩትም ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በአዲስ አበባ እየመሩ መሆናቸውን የተለጠፉ ጊዜያዊ ውጤቶች ያሳያሉ።

በከተማው እስካሁን ድረስ እየወጡ ካሉ ውጤቶች ለማየት እንደተቻለ ከብልጽግና በመቀጠል የባልደራስ ተወካዮች ሲከተሉ፣ ኢዜማ በሦስተኛነት ተቀምጧል። ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዲስ አበባ በብልጽግና እጩ እየተመሩ መሆኑም ጊዜያዊ ውጤቶች ያመለክታሉ።

በኦሮሚያ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በስፋት እየመራ ሲሆን፤ ብዙም ተወዳዳሪዎች ባለመኖራቸው ውጤቱ ልክ እንደ አማራ እና አዲስ አበባ ተጠባቂ አይደለም። ከ እናት ፓርቲ እና ከኢዜማ ተወካይ ጋር በበሻሻ የተወዳደሩት ጠቅላይ ሚ/ር አቢይ አህመድ በስፊ ልዩነት እየመሩ መሆኑን ጊዜያዊ ውጤቱ ያሳያል።
በኦሮሚያ ክልል በኢሉ አባቦራ ዞን፣ በመቱ ወረዳ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በግል የተወዳደሩት ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ከብልጽግና ፓርቲ ተተፎካካሪ የተሻለ ድምጽ አግኝተው እየመሩ እንደሆነ ጊዜያዊ ውጤቶች ያመልከታሉ።
በቤኒሻንጉል ጉምዝ አሶሳ ሁሐ እና አሶሳ መንጌለ የምርጫ ክልሎች በሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ መሰረዙን የጀርመን ድምፅ የክልሉን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ ጠቅሶ ዘግቧል።
የምርጫ ክልሎቹ በሚገኙት 102 የምርጫ ጣቢያዎች የድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረት በመከሰቱ ነው ምርጫው የተሰረዘው።

የአዲስ አበባ ህዝብ የሚወስነውን ውሳኔ እቀበላለሁ ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አስታወቀ፡፡
————————–
ይህንን ለአሐዱ ያረጋገጡት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የምርጫ ክልል 20 ፓርቲያቸውን በመወከል ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩትና ወረዳ 6 አልማዝዬ ሜዳ የምርጫ ጣቢያ 02 ድምፃቸውን የሰጡት የቢሮው ሀላፊ አቶ ገለታው ዘለቀ ናቸው፡፡
አቶ ገለታው እንደሚሉት ፓርቲያቸው የቅድመ – ምርጫው ሂደቱ አነስተኛ የተባለውን መስፈርት እንኳን ያላሟላ ነው፡፡ አሐዱ የቅድመ – ምርጫው ሂደት በዚህ መልኩ ከገመገማችሁት ለምን በምርጫው ትወዳደራላችሁ የሚል ጥያቄ አንስቶላቸዋል፡፡
የፓርቲው የቢሮ ሀላፊ ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ ራስን ከምርጫ ማግለል መፍትሔ እንዳልሆነ ጠቅሰው አንድ ምርጫ የሚለካው ደግሞ በቅድመ – ምርጫው ሂደት ብቻ ሳይሆን በምርጫው ቀንና በድህረ ምርጫው ነው ብለዋል፡፡
ትናንት ሰኞ የተካሄደውን ምርጫ ተከትሎ የአዲስ አበባ ህዝብ የሚወስነውን ውሳኔ ፓርቲያቸው እንደሚቀበል ለአሐዱ አረጋግጠዋል፡፡
ፓርቲያቸው በአዲስ አበባ ባሉ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ታዛቢዎችን እንዳሰማራም ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡