ሕወሓት በመቀሌ በአየር ተደበደብኩኝ ሲል ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ አለቀሰ | ሕወሓት በኮን፣ በጭፍራ፣ በውጫሌ፣ አርቢት፣ ጋሸና ሰላማዊ ሰዎች ላይ ሕወሓት ሰላማዊ ሰዎችን በመድፍ ሲገድል ኢትዮጵያውያን ለዓለማቀፉ ማህበረሰብ ማስጮህ አልቻልንም

 

 

 

ሕወሓት በመቀሌ አዲ አቂ መሶበ አካባቢ የኢትዮጵያ አየር ኃይል በአየር ቀጠቀጠኝ ሲል ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እያለቃቀሰ ነው። የኢትዮጵያ መንግስትም ሆነ መከላከያው ስጉዳዩ ምንም ያሉት ነገር የለም።

ሕወሓት ዛሬ በመቀሌ ደረሰብኝ ያለውን የአየር ድብደባ ወዲያውኑ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በማስጮህ ትኩረት ለማግኘት ጥረት እያደረገ ሲሆን የተለመዱት አሜሪካ፣ አየርላንድ እና አጋሮቻቸው በኢትዮጵያ ላይ መጮህ ይጀምራሉ።

ሕወሓት ወደ ጭፍራ፣ ውጫለ፣ ኮን. አርቢት፣ ጋሸና ሰላማዊ ሰው ላይ መድፍ በመተኮስ በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶችን አውድሞ በመቶዎች የሚቆጠሩ ንጹሃን ዜጎችን ሰሞኑን ብቻ የገደለ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያን ይህን በማስረጃ አስደግፈን ለውጭ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ያደረግነው ጥረት እጅግ ደካማ ነው። አዲስ ተቋቋመ የተባለው የመንግስት ኮምዩኒኬሽንም ቢሆን ይህን የሕወሓት ግፍ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ያደረገው ሥራ ደካማ ነው።

ሕወሓት ገና በአየር ተመታሁ ከማለቱ የውጭ ሚዲያዎችን ትኩርት አግኝቷል። ሕወሓት ዛሬ ተደበደብኩ ባለበት መሶበ አካባቢ፤ ተራራው ላይ የኮምዩኒኬሽን መሳሪያ እየተከተለ መሆኑን ዘ-ሐበሻ ከ3 ሳምንት በፊት ዘግቦ ነበር።

መሶበ ተራራ ላይ የሚተከለው መሳሪያን በን በተመለከተ ከትግራይ ሚሊተሪ አባላት የተገኘው መረጃ እንደሚያስረዳው አንድ የግኑኝነት መሳሪያ ጁንታው እየተከለ ይገኛል። ይህ መገናኛ መሳሪያ የሀገራችንን ውስጣዊ ጉዳይ በሚያተራምሱት ሃይላት እርዳታ መሶበ ተራራ የደረሰው በተለያየ መንገድ እንደሆነም ታውቋል። ስልን ለነበር የዘገበው። በወቅቱ ባቀረብነው ዘገባም ይህ የሚተከለው መሳሪያ “ጉዳዩ ከፍተኛ የሆነ የአየር ሃይላችንን ንስር አይን እንቅስቃሴ የሚያውክ በመሆኑ በቀጣይ ሁለት ቀናት በቀጥታ እርምጃ እንደሚወሰድበት ይጠበቃል። የተተከለበት ተራራ ከዚህ በፊት በመንግስት የተለያዩ የግኑኝነት መሳሪያ የሚተከልበት መሆኑ ታውቋል።” የሚል ነበር።

ሕወሓቶችና ተላላኪያቸው ሸኔ ዛሬ በትዊተር መቀሌ ተደበደበ በሚል መረጃዎችን ስለሚያስጮሁ ኢትዮጵያውያንም ተረባርበው ሕወሓት በኮን፣ በጭፍራ፣ በውጫሌ፣ አርቢት፣ ጋሸና፤ እንዲሁም ኦነግ ሸኔ በወለጋ የፈጸማቸውን የንጹሃን ግድያ ማሳወቅ እንደኢመገባቸው ጥሪ ቀርቧል።