“በዚህ ጦርነት ከአማራ ህዝብ ጋር ሊያጫርሱን ነው፤ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው”

ደብረጽዮን ገብረሚካኤል እንቅ እንቅ እያደረገው፣ በፍርሃት ማንበብ እየተጨነቀ፣ ፈራ ተባ እያለ፣ አንዳንዴም ደፈር ለማለት እየሞከረ የተሰጠውን ንባብ እንደምንም ጨርሷታል። ከአማራ ህዝብ ሱዳን ይሻለኛል ሲል የነበረው ደብረጽዮን ዛሬ ደግሞ “በዚህ ጦርነት ከአማራ ህዝብ ጋር ሊያጫርሱን ነው፤ ሆን ተብሎ የተደረገ ነው” በሚል የአማራ ተቆርቋሪ ሆኖ ቀርቧል። ወደ ወሎ ሰላማዊ ሕዝብ መድፍ እየወረወረ ንጹሃንን ለመግደል እየሰራ፤ ለደሴና ለኮምቦልቻ ሕዝብም የትግራይ ወራሪ ሃይል ማር ይዞልህ መጥቷልና ደግፈው ተቀበለው ሲልም ይናገራል። ለብሔር ብሔረሰቦች ጥሪ አደረኩኝ በማለትም ከጎኔ ቁሙልኝ ሲል የ27 ዓመቱ የፈጸመው ግፍና መከራ ሳይበቃው አይኑን በጨው አጥቦ ውሸቱ አንደበቱን እያሳሰረው ማንበብ እያቃተው ጥሪ አቅርቧል።

Comments are closed.