Site icon www.zehabeshanews.com

የትራንፖርት ባለስልጣን አንድ ቢሮ ኃላፊ በኮብድ 19 በመታተመሙ እሱን የሚተካ ጠፍቶ ቢሮው ለአንድ ሳምንት ተዘግቶ ተገልጋዮች እየተጉላሉ ነው

መንግስት ያወጣውን መመሪያ ተከትሎ ከትራንስፖርት ባለስልጣን የፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ ደብዳቤ ጋር በተያያዘ አገልግሎት የሚጠይቁ ዜጎች በአንድ ሰው አለመኖር ምክንያት ለሳምንት እየተጉላሉ መሆኑን ተናገሩ።

ለካርድ ምዝገባ፣ ለመኪና ፕሌት፣ ከፍጥነት መገደቢያ መሳሪያ ጋር፣ ወዘተ አገልግሎቶችን ተራንስፖርት ባለስልጣን ለማግኘት በርካታ ሰዎች እንደሚጓዙ የሚገልጹት ምንጮች አንዱ አመራር በመታመማቸው የተነሳ ይህን አገልግሎት የሚጠብቁት ዜጎች እየተጉላሉ ነው። ምንጮቹ እንደሚሉት ይህ ሃላፊ በመታመሙ እሱን የሚተካም ባለመዘጋጀቱ ቢሮው ዝግ ሆኖ ከ3 ሺህ በላይ መኪኖች እርሱ ታሞ ድኖ እስኪመጣ እየተጠባበቁ መሆኑን ራሱ የትራንስፖርት ባለስልጣን ባወጣው ማስታወቂያ ላይ ተገልጿል።

በግቢው ውስጥ የተለጠፈው ደብዳቤ ይህን ይላል፡

በትራንስፖርት ሚኒሲስትር አገልግሎት ለማግኘት የሚሄዱ ሰዎች ከንደዚህ ያለው ኋላቀር አሰራር በተጨማሪ በጉቦም ተማረዋል። አንድ አስተያየት ሰጪ ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ ሲናገሩ “ጉዳይ ለማስፈጸም በመስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እና ሃላፊዎች የሚጠየቀው ጉቦ አያድርስ ነው፤ የሰውም መጉላላትም አያድርስ ነው። እንዲህ ያለው ነገር በዘራችሁም አይድረስ” ብለዋል።

Exit mobile version