የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ በትናንትናው ዕለት በኤርትራ መንግስት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አወገዘ
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ እንደነበር በመጥቀስ ተቃውሞውን ጀምሯል።
ስለዚህም የአሜሪካ መንግስትም የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ መንግስት ጠይቆ ምክንያቶችን ዘርዝሯል።
1. “ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረሰውን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ ሉዓላዊት ሀገር በሆነችው ኤርትራ ላይ ሮኬቶችን ተኩሷል። ያለው የውጭ ጉዳይ መግለጫ
2.” የኤርትራ መንግስት በግዛቱ አንድነት እና ደህንነት ላይ ለተቋጣው ጥቃት ምላሽ የመስጠት ሉዓላዊ መብት አለው።
3. የኢትዮጵያ መንግስት የኤርትራ ጦር ግዛቱን አልፎ መገኘቱን አስመልክቶ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ቅሬታ አለማቅረቡንም መግለጫው አስታውሶ
እንዲህ ዓይነት ቅሬታ የማቅረብ መብት ያለው ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት ብቻ እንጂ ሌላ አካል አይደለም።
4. የኤርትራ መንግስት የኢትዮጵያ መንግስት ያወጀውን የተናጥል የሰብአዊ መብት ተኩስ አቁም ተከትሎ ወታደራዊ ሀይሉን ከኢትዮጵያ ማስወጣቱም ይታወቃል። ሲል ገልጿል።
5. የኢትዮጵያ መንግስት በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን የኤርትራ መንግስት እንቅፋት ነው ብሎ አያምንም። በኢትዮጵያ እና በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ያለው የሰላም ስጋት የህወሓት ጠብ አጫሪነት እና ወረራ ነው።
የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህወሓትን የማተራመስ ሚና አጥብቆ ለማውገዝ አለመፈለጉም የሽብር ቡድኑን አበረታቶታል ብሎ መንግስት ያምናል።” ብሏል።