Archive

Category: Features

የዘሀበሻ የእለቱ 5 አጫጭር ዜናዎች!

  የዘሀበሻ የእለቱ 5 አጫጭር ዜናዎች! 1 ካልቪን ክሌይንና ቶሚ ሂልፊገር የተሰኙትን ታዋቂ የልብስ ብራንዶች የሚያመርተው ፒቪኤች ኮርፖሬሽን ከመጪው ሰኞ አንስቶ ከኢትዮጵያ ምርት መቀበል እንደሚያቆም አስታወቀ፡፡ ድርጅቱ ላለፉት አምስት አመታት በሀዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ ውስጥ ፋብሪካ የነበረው ሲሆን ይህንን ፋብሪካ ሰኞ እንደሚዘጋውም ገልጿል፡፡ በፋብሪካው ውስጥ ያለውን ንብረት ቀደም ብሎ ለአንድ ኢትዮጵያዊ…

ጠረፋማ በሆኑ አካባቢዎች ሰርገው የገቡ የአሸባሪው ህወሓት ተላላኪዎች ተደመሰሱ | በርካቶችም ለጥፋት ከያዟቸው የጦር መሳሪያዎች ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል

ሀገር የማፍረስ እቅድ ይዞ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠረፍማ አከባቢዎች ሰርገው የገቡ የአሸባሪው ህወሃት ተላላኪዎች ሲደመሰሱ ብዛት ያላቸው የጥፋት ታጣቂዎች ከያዙት የጦር መሳሪያ ጋር በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ አሸባሪዎቹን ለመደምሰስና በቁጥጥር ስር ለማዋል ህብረተሰቡ ለፀጥታ ሀይሎች መረጃ በመስጠት ቁልፍ ሚና እንደነበረው ተገልጸዋል። የክልሉ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መምሪያ…

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን አነጋጋሪ ጥያቄ ሆኗል

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ሰኞ ኬንያ እገባለሁ ብለው አስነግረው ዛሬ ሮብ ናይሮቢ ደርሰዋል፡፡ ሚኒስትሩ በዚህኛው ጉብኝታቸው ሁለት ቀናት ብቻ  ይዘግዩ እንጂ ወደአፍሪካ ለመሄድ ካቀዱ በርካታ ወራትን ከማስቆጠራቸው አንፃር መዘግየት አዲሳቸው አይደለም፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አፍሪካን እንደሚጎበኙ በመጀመሪያ ያስነገሩት በነሀሴ ወር ነበር፡፡ ይሁንና ሳይታሰብ ታሊባን መላው አፍጋኒስታንን…

በዋግኸምራ በኩል ወደ ጋሸና የተሰማራው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ሙትና ቁስለኛ ሆኖ የተረፈው ተበታትኗል፡፡

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በዋግኸምራ በኩል ያሰማራው ኃይሉ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ጥምረት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበት ተመትቶ ተመልሷል። ሕዳር 8/2014 ዓ.ም ከሳመሬ ተነስቶ ወደ ጋሸና ያቀና የነበረ የትግራይ ወራሪ ኃይል በአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻ ተመትቶ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ የተረፈው ወደ ኮረም አቅጣጫ ተበታትኗል። በተመሳሳይ ዛሬ ሕዳር 9/2014…

ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካዊ ሁኔታ ከባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

የብልጽግና መንግሥት ሥልጣን ከያዘበት ከመጋቢት 2010 ዓ.ም. ጀምሮም ሆነ በቅርቡ “አዲስ መንግስት” “አዲስ ምዕራፍ” እየተባለ ከሚነገርለት ከመስከረም 24/2014 ዓ.ም. በኋላ ባለው ጊዜ መንግስት ሊሠራቸው የሚገቡ ዋንኛ ተግባሮችን ሲያከናውን አልታየም፡፡ እነዚህም የሃገርን ሉዓላዊነት ማፅናት፣ የህዝብን ሰላምና ፀጥታ ማስከበር፣ የሕግ የበላይነትን ማስፈን እና የሃገርን የኢኮኖሚና የማህበራዊ ሕይወት ማረጋጋት ናቸው፡፡ ብልጽግና ከነዚህ አንዱንም…

የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ በኢትዮጵያ ጉዳይ ከጋዜጠኞች ጋር አስገራሚ ፍጥጫ ገጠማቸው

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ቃል አቀባዩ ኔድ ፕራይስ ትላንት ማምሻውን በሰጡት መግለጫ የሰብአዊ እርዳታው እንቅስቃሴ መገደብ እንደሌለበትና እርዳታ የጫኑ መኪናዎች ወደትግራይ ክልል ሊተላለፉ እንደሚገባ አበክረው አሳስበዋል፡፡ እነዚህ መኪናዎች እንዲጓጓዙ የኢትዮጵያ መንግስት መፍቀድ እንዳለበትም ጠይቀዋል፡፡ ስለእርዳታው ሁኔታ ተጠይቀው ይህንን መሰል ምላሽ በመስጠት ላይ የነበሩት ኔድ ፕራይስ ቀጠል አድርገው አጀንዳ በመቀየር በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ውስጥ…

“በአሜሪካ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን መራጮች በቨርጂኒያ ምርጫ ለባይደን መልእክት አስተላልፈዋል” – ዘ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ዘ ዋሽንግተን ፖስት ጋዜጣ ‹‹በአሜሪካ ኢትዮጵያዊያን አሜሪካዊያን መራጮች በቨርጂኒያ ምርጫ ለባይደን መልእክት አስተላልፈዋል›› ሲል ዘግቧል፡፡ ጋዜጣው በቨርጂኒያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መራጮች ለምን ለዩንግኪን ድምፃቸውን ሊሰጡ ቻሉ? ይህስ እንዴት በሌሎች ቦታዎች ለዲሞክራቶች ችግር ሊፈጥር ይችላል? በማለት ሰፊ ትንታኔ አስነብቧል፡፡ በትንታኔው ግርማ መኮንን የተባለውን ኢትዮጵያዊ ጠቅሶ ይህ ሰው ራሱን የዲሞክራቶች ታማኝ…

የኬኒያው ፕሬዚዳንት በኢትዮጵያ ላይ እነዚህን ነገሮች ሲያደርጉ ከርመው ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል

(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኬንያው ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታ በባይደን አስተዳደር ወደኋይት ሀውስ የተጠሩ መጀመሪያው የአፍሪካ ፕሬዝደንት መሆናቸው ይታወሳል፡፡ ይህንን ተከትሎ ሰሞኑን የአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት በኬንያ መመላለስ ማብዛታቸው የሚታወቅ ሲሆን በመጪው ሰኞ የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከንም ናይሮቢ ይገባሉ፡፡ አሜሪካ ከኬንያ ጋር እንዲህ አይነት የቅርብ ትስስር የፈጠረችው ከኢትዮጵያ ጋር በተገናኘ እንደሆነ የአደባባይ…

የኢትዮጵያ መንግስት አሜሪካ በትናንትናው ዕለት በኤርትራ መንግስት ላይ የጣለችውን ማዕቀብ አወገዘ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ የአሜሪካ ውሳኔ በግልጽ የሚታወቁ እውነታዎችን ከግምት ውስጥ ያላስገባ እንደነበር በመጥቀስ ተቃውሞውን ጀምሯል። ስለዚህም የአሜሪካ መንግስትም የሚከተሉትን እውነታዎች ከግምት ውስጥ እንዲያስገባ መንግስት ጠይቆ ምክንያቶችን ዘርዝሯል። 1. “ህወሓት በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰሜን ዕዝ ላይ ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ያደረሰውን ያልተጠበቀ ጥቃት ተከትሎ ሉዓላዊት…

የዘ-ሐበሻ ዜና እና መረጃዎችን እንዴት በቪድዮ ማግኘት ይቻላል?

የዘ-ሐበሻ ዜና እና መረጃዎችን እንዴት በቪድዮ ማግኘት ይቻላል?