የ39 አመቷ ሩት ነጋ ከአይሪሻዊ እናቷና ከኢትዮጵያዊው አባቷ ዶክተር ነጋ…

በ20ኛው ክፍለ ዘመን ከነበሩ ተፅእኖ ፈጣሪ ሴት የመዝናኛ ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች መካከል ጆሴፊን ባከር አንዷ ናት፡፡

የዚህች ሴት ታሪክ በተከታታይ ድራማ መልክ እንዲሰራ ከኤቢሲ ቴሌቪዥን ጋር ስምምነት የተደረሰ ሲሆን በዚህ ፕሮጀክት ውስጥ ሩት ነጋ ተካታለች፡፡ ‹‹ጆሴፊን›› በሚል ርእስ በሚሰራው በዚህ ተከታታይ ፊልም ላይ የዋናዋን የጆሴፊንን ገፀ ባህርይ ተላብሳ እንድትጫወት የተመረጠችው ሩት በተጨማሪም ከፊልሙ ሶስት ኤክስኪዩቲቭ ፕሮዲውሰሮች አንዷ ሆና መመደቧን ዴድላይን ዘግቧል፡፡

የ39 አመቷ ሩት ነጋ ከአይሪሻዊ እናቷና ከኢትዮጵያዊው አባቷ ዶክተር ነጋ በአዲስ አበባ ተወልዳ ያደገች ሲሆን አባቷ በመኪና አደጋ ህይወታቸው ህይወታቸው ካለፈ በኋላ በአየርላንድ መኖር የጀመረች ምርጥ ተዋናይት ናት፡፡ በትወና ጥበብ ዲግሪ ያላት ይህች ኢትጵያዊ አይሪሻዊት በርካታ ፊልሞች ላይ ከመተወኗም በላይ የተለያዩ ሽልማቶችን አግኝታለች፡፡