በዋግኸምራ በኩል ወደ ጋሸና የተሰማራው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ሙትና ቁስለኛ ሆኖ የተረፈው ተበታትኗል፡፡

አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በዋግኸምራ በኩል ያሰማራው ኃይሉ በአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ጥምረት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶበት ተመትቶ ተመልሷል። ሕዳር 8/2014 ዓ.ም ከሳመሬ ተነስቶ ወደ ጋሸና ያቀና የነበረ የትግራይ ወራሪ ኃይል በአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻ ተመትቶ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ የተረፈው ወደ ኮረም አቅጣጫ ተበታትኗል።
በተመሳሳይ ዛሬ ሕዳር 9/2014 ዓ.ም አበርገሌ አካባቢ የነበረውን ኃይሉን አሰባስቦ ከሰቆጣ ወደ ቀውዝባ አሰፍስፎ ሲመጣ ተደምሷል።
የራያ ፋኖ እና ጢነኛ በመቀሌ አላማጣ ቆቦ ወልድያ መስመር እንዳያልፍ የእግር እሳት የሆነበት የትግራይ ወራሪ ኃይል፣ የመቀሌ አበርገሌ ሰቆጣ ላሊበላ ወልድያ ደሴ መንገድ በዋግ ትንታጎች ተቆርጦበት መውጫ አጥቷል።
በዋግኸምራ ግንባር በርካታ አካባቢዎች በአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻ ቁጥጥር የገቡ ሲሆን የትግራይ ወራሪ ኃይል የሚያደርጋቸው ስምሪቶች በተደጋጋሚ እየከሸፉበት እንደሚገኝ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል።

Comments are closed.