ትህነግ በተንቤን ትላንት ማታ ጁንታው እሩጠው ያልጠገቡ ህፃናትን ሰባስቦ ውጊያ ከፍቶ ነበር

አዳም ብርሃን እንደፃፈው:-
ትህነግ/ህውኃት ከምርጫው በፊት ያለችውን እንጥፍጣፊ ሀይል አሰባስቦ፣ ትላንት አመሻሹ ላይ ተንቤንን ለመውረር ሞክሯል። በተንቤን ትላንት ማታ ጁንታው እሩጠው ያልጠገቡ ህፃናትን ሰባስቦ ውጊያ ከፍቶ ነበር።

ነገር ግን ሰዓታት ሳይዋጋ ከ11 በላይ ኮሎኔልና ጀነራቹን አስደምስሶ ጎዞው በአጭር ተቋርጧል። በጣም በሚገርም ሁኔታ ውጊያው ከመጀመሩ ያልጠበቁት ዱላ ሲደርስባቸው ተደናግጠው እጅግ ብዙ የጁንታው ታጣቂዎች እጃቸውን ለመከላከያ የሰጡ ሲሆን፣ ከነዚህ ውስጥ 64ቱ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች ናቸው።
ከተማረኩት ውስጥ ብዙ ቁጥር ያላቸው በጫካ ያረገዙ ሴት እህቶች እና በኪሳቸው ኮቾሮ ብስኩት ሳይሆን ሀሽሽ በብዛት የያዙ ወጣቶች እንደሚበዙ ሌሊት መረጃውን ያቀበለኝ ወዳጄ አረጋግጦልኛል።

ህፃናቱን ከእድሜያቸው የሚጠበቀው #የልጅነት_ፍርሃት እንኳን እንዳይሰማቸውና በደመ-ነፍስ እሳት ውስጥ እንዲገቡ አደንዛዥ እፅ ያስጨሷቸዋል፣ በእፅ የደነዘዙት ህፃናት እሳት መግባታቸው ሳያንስ እርስ በርስ ጥንቃቄ የጎደለው ፆታዊ ግንኙነት በመፈፀማቸው፣ እጅግ ብዙ ሴት ልጆች ከተደበቁበት ሲያዙ ወይም እጃቸውን ሲሰጡ ነድሰ-ጡር ሁነው ይገኛሉ።

በትላንቱ የተንቤኑ ውጊያ የጁንታው ተዋጊ ወታደሮች ስላለቁ፣ ህፃናት፣ አክቲቪስቶችና ነፍሰ ጡር ሴቶች ናቸው የተሰለፉት። ከሞላ ጎደል እጃቸውን የሰጡ ሲሆን፣ ዋና ዋናዎቹ ኮሬኔልና ጀነራሎች ግን ተደምስሰዋል።

መከላከያችን የኢትዮጵያ ክንድ ነው!!
ኢትዮጵያ ትደቁሳለች!!