አርቲስት አልጣሽ ከበደ በስእሉ አለም ካሉ አምስት ጥቁር ሴቶች አንዷ ሆነች፡፡

አርቲስት አልጣሽ ከበደ በስእሉ አለም ካሉ አምስት ጥቁር ሴቶች አንዷ ሆነች፡፡

ታዋቂው ፎርብስ መፅሄት ‹‹በስእሉ አለም ሊያውቋቸው የሚገቡ አምስት ሴቶች›› በሚል ርእስ ባቀረበው ዘገባ ውስጥ አልጣሽ ከበደን አካቷታል፡፡

ይህንን ዝርዝር የመረጠው አንጋፋው አፍሪካ አሜሪካዊው የስእል ባለሙያና አማካሪ አላኒያ ሲሞን ነው፡፡ ፎርብስ ስለ አልጣሽ ሲናገር ‹‹በሎስ አንጀለስ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረ ጋለሪ ያላት፣ በአሁኑ ወቅት ለኮርፖሬሽንና ለግለሰብ ደንበኞቿ የማማከር አገልግሎት የምትሰጥና በአሜሪካና በመላው አለም በሚገኙ ሙዚየሞች እየተዘዋወረች የስእል ስራቆቿን ያቀረበች ናት›› ብሏል፡፡

ሲሞን ምስክርነት ሲሰጥላት ደግሞ ‹‹አልጣሽ ከበደ የመጀመሪያ የስእል ጨረታዋን በ2008 ያቀረበችው በአፍሪካ ዲያስፖራ ኤግዚቢሽን ወቅት ነበር፡፡ የእሷ ስራዎች በስእል ገበያው ውስጥ አይኔን እንድከፍት አድርጎኛል፡፡ ከዚያን ጊዜ ወዲህ የጥቁር አርቲስቶች የስእል ስራ በጨረታዎች ላይ ዋጋው ሊጨምር ችሏል፡፡›› በማለት በፎርብስ መፅሄት ላይ ፅፏል፡፡

አልጣሽ ተወልዳ ያደገችው በኢትዮጵያ ውስጥ ሲሆን በአፍሪካ አሜሪካዊያን የስእል ማህበረሰብ ፈር ቀዳጅና በኢንዱስትሪው ውስጥ ትልቅ ደረጃ የደረሰች ናት፡፡ ለአስር አመት ያህል የስእል ስራ ድለላ ስትሰራ ቆይታ የራሷን የስእል ጋለሪ የከፈተችው በ1994 አ.ም ነበር፡፡ ሎስ አንጀለስ በሚገኘው ጋለሪዋ የራሷንና የሌሎች ታዋቂ አርቲስቶችን ስእል ለእይታ ስታበቃ ቆይታለች፡፡