በኮሮናና በክረምቱ ጉርፍ በአፋር ክልልና አካባቢው መደበኛ እንቅስቃሴ አይታሰብም !!!

Afar

******

 በአዋሽ  ወንዝ  መሙላት  የተነሳ  ከፍተኛ  ጉዳት በመድረሱ  መንግስታዊና መንግስታዊ  ያልሆኑ ተቋማት በሙሉ ወድመዋል። በተለይም ደግሞ  በዞን አንድ እና ሶስት የኮሮና መከላከል ጉዳይ እና የ2013  ትምህርት  መጀመር  አይታሰብም።   የጤና፣ የትምህርት  ፣ የግብርና   ተቋማት በሙሉ በጎርፍ ተወሰደዋል።  በእንቅርት  ላይ ጆሮ ግድፍ  እንዲሉ በክልሉና  በአካባቢው  የካፒታል በጀት  ከዕቅድ  ወጭ  ለነፍስ አድን ሥራና  መልሶ መቋቋም ጥቅም ላይ እየዋለ  ነው ። 

ተዋቸውደርሶ 

በአሳኢታ  በኮሮዱራ ቀበሌ ህዝቡ በውሃ ተከቦ ይገኛል። በመሆኑም  በሀገር  አቀፍ ደረጃ  የእርዳታ  ጥሪ ቀርቧል  ። በተለይም   ዋና  የምትችሉ ወጣቶች ወደዚያ ለመሄድ  አዲስአበባ ፒያሳ አካባቢ   ትራንስፖርት  ስለተዘጋጀ  ሀገራዊ  ጥሪውን ተሳትፎ  ። ከበሰቃ ፣ ከከሰም ፣ ከተንዳሆ ግድቦች በሚለቀቀው ውሃ የተነሳ  በአካባቢው  መጠን ሰፊ ችግር ተክስቷል ።  በዚህም  ህዝባችን ዋጋ እየከፈልን ይገኘል ። 

ምናልባት የሞተው ሞቶ የተረፈው  ህዝብ ከዚህ በኃላ  የጎርፍ ሰለባ  የሚሆንበት  ታሪክ እንዲያከትም  የሁላችንንም  ጥረት ይጠይቃል ። ለዛፍ ተከላና ለፌሽታ የሚሆን የባከነ ሰአት የለንም።  የሰው ልጅን ህይወት በአፋር ክልል  ከጉርፍ ለማትረፍ ግብግብ  ተይዟል ።