“ጌታቸው ረዳ ከሁለት የሕወሓት ደጋፊ ድምጻውያን ጋር ሆኖ በረሃ ላይ የቆሰሉን የሕወሓት ታጋዮችን ተሳልቆባቸው በኋላ ጥሏቸው ያመለጠ ይሉኝታ ቢስ ነው”

ጌታቸው ረዳ ከሁለት የሕወሓት ደጋፊ ድምጻውያን ጋር ሆኖ በረሃ ላይ የቆሰሉን የሕወሓት ታጋዮችን ተሳልቆባቸው በኋላ ጥሏቸው ያመለጠ ይሉኝታ ቢስ ነው ሲሉ ሻምበል ሰለሞን ሁነኛው በመከላከያው  ማህበራዊ ሚዲያዎች በኩል ባሰራጩት ጽሁፍ ገለጹ።

ድምጻዊ አብርሃም ገብረመድህን ከሕወሓት ጋር መዝመቱን ከዚህ ቀደም መዘገባችን እና ድምጹም መጥፋቱን መዘገባችን የሚታወስ ነው። ጠፍቶ የነበረው ይህ ድምጻዊ ባለፈው ሳምንት ለጓደኞቹ ስልክ በመደወል በሕይወት እንዳለ መግለጹንም ዘግበናል።

ከግዳጅ ቀጣና ሻምበል ሰለሞን በላኩት ጽሁፍ ጌታቸው ረዳ፣ ድምጻዊ አብርሃም ገብረመድህን እና እምበር ተጋዳላይ በሚለው የትግረኛ የትግል ዘፈኑ የሚታወቀው አበበ አረአያ በቆላ ተምቤን ላይ 4 ቀን በፈጀው ከባድ ጦርነት የሕወሃት ኃይሎች ሲደመሰሱ የቆሰሉት ላይ ተሳልቀውባቸው ጥለዋቸው ሄደዋል ብለዋል።

ሻምበል ስለሞን እንዳሉት “በስተት እንኳን ከውሸት ውጭ እውነት ተንፍሶ የማያውቀው ጌታቸው ረዳ  በትግራይ ምዕራባዊ ዞን መደባይ ዛና ወረዳ ውስጥ ፣ በመንገዱ ማብቂያ ሜዳ ላይ ፣ ስራችሁ ያውጣችሁ ብሎ ስለተዋቸው ራሱ ያዘመታቸው  በርካታ ከባድ ቁስለኞች ግድ ሳይለው ፣ ቆላ ተንቤን ጉያ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከድቷቸዋል ።” ብለዋል።

“ከመቀሌ ጀምሮ ሲያጓጉዛቸው የነበሩትን አካል ጉዳተኛ የቀድሞ ታጋዮችን ከነቤተሰቦቻቸው ጥሎ የሸሸው ውሸታሙ ጌታቸው … ስለ ድል አድራጊነት ሲያወራ ከማዳመጥ በላይ ምን የሚደንቅ ነገር አለ?” የሚሉት ሻምበሉ “ገታቸው ረዳ ማለት”A” ደረጃ ተለይተው በሞት እና በህይወት መሀል የሚገኙ መንቀሳቀስ የማይችሉ ራሱ የላካቸው ቁስለኞች መሀል ከሙዚቀኞቹ አብርሃም ገ/መድህን እና አበበ አርአያ /የእንበር ተጋዳላይ ሞዛቂ/ ጋር ቆሞ ፣  የምትችሉ አምልጡ ብሎ የተሳለቀ ይሉኝታ ቢስ ከሀዲ ነው።” ሲሉ በቆላ ተንቤን ከድምጻውያኑ ጋር በመሆን በቆሰሉ የሕወሓት ታጋዮች ላይ የፈጸመውን ግፍ አጋልጠዋል፡

“ከምላስ ውጭ የመሳሪያ ምላጭ ስቦ የማያውቀው ይሔ ሰው ፣ መከላከያ ሰራዊቱን እያረገፍነው ነው። ድል በድል ሆነናል ወዘተርፈ እያለ ሲቀባጥር ማዳመጥ በርግጥም አስቂኝ ነው።”የሚሉት  ሻምበል ሰለሞን ሁነኛው ከግዳጅ ቀጠና “ግን ደግሞ ውሾች ይጮሃሉ ግመሎቹም ከመሔድ አልቆሙም።” ሲሉ መል ዕክታቸውን ዘግተዋል።

ኢትዮጵያችን ለዘላለም ትኑር!!