ከአንድ አመት በፊት የተከሰከሰውንና ሶስት ሰዎችን ለሞት የዳረገውን የደቡብ አፍሪካ አውሮፕላን አደጋ በተመለከተ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች ምርመራ ሊያደርጉ ነው

ከአንድ አመት በፊት የተከሰከሰውንና ሶስት ሰዎችን ለሞት የዳረገውን የደቡብ አፍሪካ አውሮፕላን አደጋ በተመለከተ የኢትዮጵያ ባለሙያዎች ምርመራ ሊያደርጉ ነው፡፡

ከኢትዮጵያ አውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ የተውጣጣ አንድ የምርመራ ቡድን በዚህ ሳምንት ወደደቡብ አፍሪካ እንደሚያቀና ተሰምቷል፡፡ አውሮፕላኑ ባለፈው አመት ጃንዋሪ 23 ቀን 2020 በረራ በጀመረ በሰከንዶች ውስጥ በአፍንጫው ተገልብጦ አንድ ተራራ ላይ መውደቁ ይታወሳል፡፡

አደጋውን በተመለከተ በወቅቱ የደቡብ አፍሪካ የትራንፖርት ሚኒስትር ፊኪል ቡላላ በሰጡት መግለጫ መንግስት የራሱን አውሮፕላን አደጋ መንስኤ ስለማይመረምር በገለልተኛ አካል እንደሚጣራ ገልፀው ነበር፡፡ ይህንን ገለልተኛ አጣሪ አካል የመምረጡ ስራ በኮቪድ 19 የተነሳ የዘገየ ቢሆንም አሁን አጣሪው ታውቋል፡፡ በዚህ መሰረት የኢትዮጵያ የአውሮፕላን አደጋ ምርመራ ቢሮ በመመረጡ በዚህ ሳምንት ወደደቡብ አፍሪካ ተጉዞ የምርመራ ስራውን አንደሚጀምር ዲስፓች ላይቭ ዛሬ ዘግቧል፡፡