የህወሓት ሊቀመንበር ጓድ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በኣዲስ ኣመት ዋዜማ ያስተላለፋት መልእክት

-2012ዓም ከባድ ፈተናዎችና ቀውሶች የገጠሙበት በህዝባችን ላይ ዘርፈ ብዙ ጉዳቶች የደረሱበት በኮቪድ -19 ምክንያት ምርጫ የተራዘመበት ነው።የትግራይ ህዝብ ግን በማንም ግዜ የሚከበረው የራስን እድል በራስ የመወሰን ህገመንግታዊ መብቱን ተጠቅሞ መሪዎች ስልጣን ላይ የሚቀመጡት በራሴ ውሳኔ እንጂ በኮሮና ሰበብ ኣይደለም በማለቱ ኮቪድ-19 በመከላከል ምርጫ ኣካሂዶ ውጤቱ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።በዚህ ኣጋጣሚ በመላው ሃገሩቷና ውጪ ሃገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን የትግራይ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብቱ ተገቢ ነው ብቻ ሳይሆን ጉዳዩ የትግራይ ህዝብ ብቻ ሳይሆን የኛም ነው ብላቹ ኣጋርነታችሁ በተግባር ስለገለፃቹ በኣስቸጋሪ ሁኔታ ሆናቹም ስለደገፋችሁን ከፍተኛ ክብር ኣለን።ትግሉ ብቻ ሳይሆን ውጤቱም የጋራችን በመሆኑ እናንተም እንኳን ደስ ኣላቹ።

Dr Debretsion Gebremichael (PHD)

-የተከበራችሁ የኢትዮጵያ ህዝቦች የትግራይ ህዝብ ምርጫ የሚወስነው የትግራይ ክልል መንግስት ህወሓት ወይም ሌሎች ፓርቲዎች ኣይደሉም።የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብት የትግራይ ህዝብ ነው።ዳኛው ይግባኝ ሰሚው የመጨረሻ ፍርድ ሰጪው የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው።ዓንቀፆች እየቆጠሩ መተርጎም ግዜ ማባከን ካልሆነ በህዝብ ውሳኔ ፊት ፋይዳ የለውም።ትግራይ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብቱ የራሱ በመሆኑ የህዝብ ውሳኔ ከመቀበልና ከማክበር ውጪ ሌላ ኣማራጭ መዳሰስ የቆጡን ኣወርድ ብላ የብብቷን ኣጣች ሊያስከትል ይሆናል እንጂ ሌላ ፋይዳ እንደሌለው መገንዘብ ያሰፈልጋል።

-በተገባደደው 2012ዓም የኣማራና የትግራይ ህዝብ ለማጋጨት የተደረጉ ሙኸራዎች ነበሩ።የመሬት ኣስመላሽ ነፃ ኣውጪ ኮሚቴዎችና ሌሎች የተፈለፈሉ በማሰማራት” ትህነግ የምትባል ፍጡር እስካለች ድረስ የኣማራ ሂወት ከምስቅልቅል ኣይወጣም” እያሉ የህዝቡ ስቃይ ለማራዘም ቢሞክሩም የኣማራ ህዝብ ማጭበርበሩ ይብቃቹ የራሳቹን ችግር ፈትሹ ከትግራይ ህዝብ ጋር ኣንጋጭም እረፋ እያለ የከፋ ጉዳት እንዳይደርስ መታገሉ ለኣማራ ህዝብ ክብር እንዳለን ለመግለፅ እንወዳለን።ለትግራይ ክልል ኣቅራቢያ ያሉት የኣማራ ህዝቦች እንደሚያውቁት በክልሉ ኣመራር የሚታገዙ ታጣቂዎች ትናንት ታሪካዊ ምርጫችን ለማደናቀፍ ያዙን ልቀቁን እያሉ የነበሩ ቢሆንም በትግራይ ህዝብና የፀጥታ ሃይሉ ፊት መቆም

የማይችሉ መሆኑ ለምስክር መቅረብ ይችላሉ።

-የኣማራ ክልል ኣመራር በ2013ዓም ኣፋቹንና ሚድያችሁን ስለ ትግራይ ማውራቱን የሚያቆምበት ኣመት እንደሚሆን ተስፋ እናደርጋለን።ስለራሳችሁ ምታስተዳድሩት ህዝብ በማሰብ ማገልገል ጀምሩ።ወይም ማገልገል ለሚችሉ ያለ ምንም ግርግር

ስልጣናችሁን ልቀቁ።2013ዓም በህዝብ ሂወት ኑሮና ጊዜ መቀለድ የሚቆምበት ኣመት ይሆናል ብለን እንመኛለን።በትግራይ ህዝብ ላይ ከውጭ ሃይሎችም እየተባበራቹ ሁሉም ኣይነት ግፍ እየፈፀማቹ የምትገኙ የድሮና ኣዳዲስ ኣሃዳውያንና ሌሎች ተስፈኞች እና ተላላኪዎችና ከተላላኪዎች በታች የሆናቹ ሁሉ ማሳወቅ የምንፈልገው የትግራይ ህዝብ የማያከብር ጨው ለራሱ ብሎ ይጣፍጥ ነው።