ከጋሸና ላሊበላ መስመር ላይ ባለችው ዳቦ ከተማ ተነስተው የመጡ የሕወሓት ታጣቂዎች አስከሬናቸው ሜዳ ላይ ቀረ | አንቺም ድርቀ ሰፋያት ላይ ከ500 የማያንሱ የአሸባሪው ታጣቂዎች ዶግ አመድ ሆኑ

 

በጋሸና ግንባር የኢትዮጵያ ሃይሎች አንጸባራቂ ድል በአሸባሪው የህወሓት ኃይል ላይ እየተቀዳጁ መሆኑን የዘ-ሐበሻ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል። ጋሸናን በቁጥጥር ስራቸው አውለው ወደ ላሊበላ መስመር ላይ ባለችው ዳቦ ከተማ ላይ ውጊያ እያካሄዱ የሚገኙት የኢትዮጵያ ኃይሎች ሕወሓት በየጊዜው እያመጣ የሚጨምራቸውን ታጣቂዎች በመደምሰስ አሁንም አንጸባራቂውን ድል በመድገም ላይ ናቸው።

በላሊበላና በጋሸና መስመር ላይ በምትገኘው ዳቦ ከተማ ተነስተው ለቆረጣ የተላኩ 36 የሚሆኑ የሕወሓት ታጣቂዎች በኢትዪጵያ ኃይሎች እርምጃ ተወስዶባቸው አስከሬናቸው ሜዳ ላይ ተሰጥቷል። በተጨማሪም አንቺም ድርቀ ሰፋያት ላይ ሕወሓት ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት ይዞ የመጣ ሲሆን በዚህ አካባቢ በተደረገው ውጊያም ከ500 የማያንሱ የሕወሓት ታጣቂዎች ዶግ አመድ ሆነዋል። በዚህ አካባቢ የቆእስለና እጁን የሰጠው የሕወሓት ታጣቂ ብዛት በርካታ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በሰላም እጃቸውን የሰጡትን የኢትዮጵያ ኃይሎች ተንከባክበው ወደ ምርኮኛ ጣቢያዎች አጓጉዘዋቸዋል:
ይህ በእንዲህ እንዳለም ጣጃ ትምህርት ቤት አካባቢ ሆኖ ለአሸባሪውና ወራሪው የሕወሓት ኃይል ሽፋን በመስጠት ወደ ሰላማዊ ህዝብ ላይ ጭምር ሲተኩስ የነበረው ከባድ መሳሪያም የኢትዮጵያ ኃይሎች በመድፍ መትተው ይህን ከባድ መሳሪያ አውድመውታል።

በአጠቃላይም በጋሸና ግንባር አሸባሪውና ወራሪው የሕወሓት ኃይል ከፍተኛ የሆነ ሽንፈትን እየተከናነበ እንደሚገኝ የመከላከያው ምንጭ ለዘ-ሐበሻ ተናገረዋል።