የትግራይ መከላከያ ቃል አቀባይ ነኝ የሚለው ገብረ ገብረጻድቅ አገኘነው ያለው 3 የድል ዜና ሕልም አይከለከልም የሕወሓት ምላስም አይሞትም የሚለውን የሚያስታውስ ነው ተባለ

ራሱን የትግራይ መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ ነኝ የሚለው ኃይል ገብረ ገብረጻድቅ ዛሬ በድምጺ ወያኔ በድምጽ ተቀርጾ ባስተላለፈው መል ዕክት የትግራይ መከላከያ ሰራዊት ከአክሱም ወደ አዴት ሲጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አንድ ሻለቃ ጦርን ሕደግ ውረድ የተባለ አከባቢ ሙሉ በሙሉ ደመሰስኩ የሚልና ተጨማሪ የድል ዜናዎች በሚል ያሰራጨው መረጃ ፍጹም ሃሰት እንደሆነና በአካባቢው ምንም ነገር እንደሌለ አንድ የዘ-ሐበሻ የመከላከያ ምንጭ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::

ራሱን የትግራይ መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ ነኝ ብሎ የሚጠራው ገብረ ገብረጻድቅ የተናገረውን ለግንዛቤ እናስደምጣችሁና ለዘ-ሐበሻ የደረሰውን መረጃ እናስከትላለን::

ሕወሓት በአንድ በኩል በውጭ ሃገር ጦርነት ይቁም የሚል ዜና ሰልፈኞችን አሰልፋ ትጠይቃለች:: በሌላ በኩል ሰላማዊ ሰዎች ተገድሉብኝ እያለች ትጮሃለች በአንድ በኩል ደግሞ ደመሰስኩ ትላለች የሚሉት እኚሁ የመከላከያ ምንጭ እነ ገብረ ጻድቅ አክሱም አካባቢ ደመሰስነው እያሉ የሚናገሩት ሻለቃ በተጠቀሰው አካባቢ እንዳልነበረ ይገልጻሉ:: እነርሱ ደመሰስነው የሚሉት ሻለቃ በተሰጠው ግዳጅ ሆኖ የሕዝብን ሰላም ከማስጠበቅ ውጭ ምንም እንዳልገጠመው ይገልጻሉ:: እንደውም በአካባቢው የሕወሓት ሚኒሻ ትጥቅት በመፍታቱና እንዲሁም አለ የሚባለው የተቆረጠ ሰራዊትም ባለመኖሩ  ሰራዊቱ ወደ ተሽካሪ ጥገናዎች ፊቱን አዙሮ ነው የከረመው ብለዋል::  በዚህ ዕዝ ክፍለ ጦር ጥገና ክፍል ሰራዊቱ ለግዳጅ የሚጠቀምባቸው ተሽከርካሪዎች ብልሽት እንዳያጋጥማቸው የቅድመ መከላከል ስራ በመስራት;  ከሻለቃ ጀምሮ እስከ ክ/ጦር ያሉ ተሽከርካሪዎች ለሰራዊቱ መስጠት የሚገባቸውን ግልጋሎት እንዲሰጡ ሰራዊቱ በተሰማራበት የግዳጅ ቀጣና ሁሉ በመንቀሳቀስ የመከላከል ጥገና በመስራት ላይ ነው የከረመው የሚሉት ምንጩ ሕወሓት ውሸት የማሰለቸው ድርጅት ነው ብለዋል::

ምንጩ እንደሚሉት ሕወሓት እንዲህ ያሉ የደፈጣ ውጊያዎችን እያደረኩ ነው- ድልም አገኘሁ – ደመሰስኩ እያለ መረጃ የሚለቀው የዓለም መንግስታት ጦርነቱ አያልቅም ብለው እንዲያስቡ እና ወደ ድርድር እንዲያስገቡት ነው::  በቆላ ተንቤን የነበረው የሕወሓት ኃይል ሙሉ በሙሉ ተደምስሶ አጠራቅሞት የነበረው መድሃኒትና የመሳሪያ ክምችት በቁጥጥር ስር መዋሉን ያስታወሱት ምንጩ በአንዳንድ አካባቢዎች አሁንም የተቆራረጠ የሕወሓት ሰራዊት ቅሪት እንዳለ ገልጸው እንኳን ሻለቃ የመደሰስ ኃይል ሊኖረው ይቅርና እግሬ አውጪኝ እያለ ከቦታ ቦታ እየፈረጠጠ የትግራይን ገበሬ እየዘረፈ ነው ሲሉ ተናግረዋል::

የትግራይ መከላከያ ቃል አቀባይ ነኝ የሚለው ገብረ ገብረጻድቅ የትግራይ ሕዝብ ድጋፍ እያደረገልን ነው ሲሉ ቢናገሩም የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ሪር አድሚራል ክንዱ ገዙ በ‹‹ዘመቻ ለፍትህ›› የፎቶ ውደ ርዕይ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ “ሕወሓት በሰሜን ዕዝ ላይ የመጀመሪያውን ጥቃት ከፈጸመ ዕለት ጀምሮ ያ  ሁሉ በደልና ጥቃት ሲደርስብን የትግራይ ህዝብ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ያለውን ሚና ሳያነሱ ማለፍ ደግሞ ተገቢ አይደለም፤

? የትግራይ ህዝብና ህወሓት አንድ ናቸው የሚለው የህወሓት ትርክት ፉርሽ መሆኑ የተረጋገጠው በዚህ ጦርነት ነው ብዬ አስባለሁ፤ 

? የትግራይ አርሶ አደሮች እንዲሁም የከተማዋ ነዋሪዎች በሠራዊታችን ላይ አንድ ጥይት አልተኮሱም፤ 

? የወለደች የወታደር ባለቤት መኖሯን የሰሙ የከተማዋ ነዋሪዎች ተሰባስበው ለአራሷ የሚገባትን አድርገው ካምፕ ላይ ጥቃት እንዳይደርስብሽ ብለው ቤታቸው ወስደዋታል፤

? በትግራይ ሕዝብና በህወሓት መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ያስፈልጋል፤ ህወሓት መሸሸጊያ ላደረገው የትግራይ ሕዝብ አንድ እና ያው ናቸው የሚለው ትርክት ሕዝብን በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ እድሜ፣ ወርድና ቁመት የሚለካ ፀረ ሕዝብ እሳቤ መሆኑ በተግባር ታይቷል፤” ሲሉ ዛሬ ተናግረዋል::