የሐገር መከላከያ ሰራዊት የ31ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ በነበረው ጀኔራል ከበደ የሚመራው የጁንታው የተቆራረጠ ሀይል አምባለጌ ላይ ቀለበት ውስጥ ገብቷል

የሀገር መከላከያ ሰራዊት የ31ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ የነበረው ጀኔራል ከበደ የሐገር መከላከያ ሰራዊቱን ከድቶ ከጁንታው አባላት ጋር ተቀላቅሎ በአምባላጌ ተራሮች ላይ ከጁንታው አባሎች ጋር ተከቧል።

ላለፉት አራት ቀናት በጀኔራል ከበደ የሚመራው የተቆራረጠ ሀይል ከመከላከያ ሰራዊቱ ጋር ያደረገው ጦርነት በሎጂክ ችግር ምክንያት በሐገር መከላከያ ሰራዊት እየተመታ ይገኛል።

በአምባላላ ተራሮች የሐገር መከላከያ ሰራዊት እየወሰደ ባለው እርምጃ ጀኔራል ከበደና የትህነግ ከፍተኛ አመራር የነበሩ አመራሮች ጭምር እንደተከበቡ እየተነገረ ነው።

በስፍራው ያሉ አንድ የጦር መኮንን እንደገለፁት የሐገር መከላከያ ሰራዊት በጀኔራል ከበደ የሚመራው የተቆራረጠ ሐይል በሁሉም አካባቢ ተከቦ ማምለጥ በማይችልበት ሆኔታ ውስጥ እንደገባ ተናግረዋል።