“በዚህ ቁመና ላይ ሆነን ፣ ጁንታው ነገ እንገባለን…የአስር ብር ርቀት ላይ ነን…ደግሳችሁ ጠብቁን የሚል ፕሮፓጋንዳ ቢነዛም ህዝቡ አይደናገርም ” – ሜ/ጀ ክንዱ ገዙ

ራሱን የሕወሓት የሽፍታ ቡድን ቃል አቀባይ ነኝ የሚለው ገብረገብረ ጻድቃን በድምጺ ወያኔ ላይ በድምጽ ከጠፋ ቆይቷል። ሆኖም ግን ድምጺ ወያኔ ገበረገብረጻድቃን የድል ዜና ነገሩኝ እያለ በሰበር ዜና መናገሩን ቀጥሏል። ዛሬም የገብረገብረጻድቃን ድምጽ በሌለበት ዘገባው የተለያዩ የድል ዜናዎችን ለደጋፊዎቹ አሰምተዋል። ሚያዝያ 15 እና ሚዚያ 16 በዕዳጋ አርጊ ነበለት፤ በዓዴት፣ በአግበ’ጅጅቀ፣ በተንቤን ጉያ በስንቃጣ ሓውዜን ድል እንደቀናው ተናገረ ተብሎ በገበረ ስም መግለጫ ወጥቶ በሰበር ዜና ተነግሯል።

General Kindu Gezu

ዘ-ሐበሻ ወደ መከላከያ ምንጮች በደመደወል የተለያዩ መረጃዎችን ለማግኘት ሞክሯል። ሕወሓት የሽፍታ ሥራውን መቀጠሉን የገለጹት አንድ የመከላከያ ምንጭ በተለያዩ አካባቢዎች አሁንም ትንኮሳ መፈጸሙ እንደቀጠለ ቢሆንም ከ3 ቀን በፊት ብቻ በቆላ ተንቤን አካባቢ የሽፍታው ቡድን አዳዲስ ኃይሎችን በማደራጀት ውጊያ ከፍቶ ከነበረው ውጭ የሚጠቀስ ሌላ ከበድ ያለ ነገር የለም ብለዋል።  በቆላ ተንቤን አካባቢ በተደረገው ውጊያ በርካታ በግድ ወደ ጦርነት የገቡ አዳዲስ የሕወሓት ታጣቂዎች እጅ መስጠታቸውን የሚገልጹት ምንጩ፤ እነዚሁ የተማረኩ ወታደሮች እንደተናገሩት “ጓደኞቻችን ተመተው ሲቆስሉ ምንም የህክምና መስጫ ስለሌላቸው የቆሰሉትን ገድለዋቸው ሄደዋል” ሲሉ ተናግረዋል።

የሕወሓት ታጣቂዎች በቅርቡ ወደ አማራ ክልል ዋግ ህምራ ዞን በመግባት በርካታ ሰላማዊ ሰዎችን እና ሚኒሻዎችን በመግደል የህክምና እቃዎችን ዘርፎ መሄዱ የሚታወስ ነው።

ገጠር ያለው የትግራይ ገበሬም እጅጉን እየተጉዳና እያማረረ መሆኑንም እኚሁ የመከላከያ ምንጭ ገልጸዋል። የሕወሓት ሽፍታ ታጣቂዎች ምግብ ስሌላቸው የገበሬውን ዘርፈው እንደሚሄዱ፤ ተመተው ሲደበቅ ደግሞ ምግቡን ጥለው ስለሚሄዱና ሲመለሱ ይህን ስለማያገኙት በተደጋጋሚ ገበሬውን ልጁንም ምግቡንም እየዘረፉት ነው ተብሏል። ልጆቻችንን ቀምተው መውሰዳቸው ሳያንስ የአደንዛዥ ዕጽ ተጠቃሚ አደረጓቸው እያሉም እያማረሩ ነው።

ከዚህ ቀደም ከተማረኩ የሕወሓት ታጣቂዎች ኪስ ውስጥ ሃሺሽ እንደሚገኝ ጄነራል መሀመድ ተሰማ መግለጻቸው አይዘነጋም። አሁንም ሕወሓቶች ምን ያህል ሃሺሽ እንዳላቸው ባይታወቅም ከሚማረኩት ኪስ ውስጥም ሆነ ጥለውት ከሸሹት መደበቂያ ጢሻ ውስጥ ሃሺሽ በብዛት እየተገኘ ነው።

ሽፍታውው በየጊዚው የሚነዛውን ፕሮፓጋንዳ በማስመልከትም የሰሜን ዕዝ ከፍተኛ አመራር ሜ/ጀ ክንዱ ገዙ : “ጁንታው ማሸነፍ ቢችል ኖሮ ፣ ማሸነፍ የነበረበት ጦርነቱን ባጠቃላይ በኢትዮጵያ ፣ በተለይም በሰሜን ዕዝ ላይ በከፈተበት ጊዜ በነበረው አቅም ነበር ማሸነፍ የሚችለው – ቢችል ኖሮ ፡፡ግን ይዞት የተነሳው ፍትሀዊ ያልሆነ ዓላማ ስለነበረ ጥቅምት 24 ጦርነቱን በራሱ ተነሳሽነት ሲጀምር የነበረውን አቅም ይዞ እንኳን ሶስት ሳምንት መቆየት አልቻለም ፡፡ ጦርነቱ ሲጀመር ጁንታው በመቶዎች የሚቆጠሩ ታንኮቻችንን ፣ መካከለኛና ረጅም ርቀት ሚሳዔሎቻችንን ይዞ ነበር ፡፡ በደንብ የተደራጀ ፣ የታጠቀ ፣ የአመራር ሰንሰለት ያለው ፣ የግንኙነት ስርዓት እና ሪሶርስ እንዲሁም ከ80ሺ በላይ ሊዋጋ የሚችል ሀይል ነበረው ፡፡ ታንክ ፣ መድፍ ፣ ብረት ለበስ ፣ ሚሳዔል ይዞ በስብከቱ ዓላማ ልክ የተሰለፈ 80 ሺ የሚዋጋ ሀይል ቢይዝም እንዳልነበረ ሆኗል ፡፡ አብዛኞቹን ታንኮቻችንን ፣ ብረት ለበሶቻችንን ፣ መድፎቻችንን በውጊያ ሂደት ወደ ሀይል መልሰናል ፡፡ የጎደለንን የሰው ሀብት በአጭር ጊዜ አሟልተናል ፡፡ በዚህ ቁመና ላይ ሆነን ፣ ጁንታው ነገ እንገባለን…የአስር ብር ርቀት ላይ ነን…ደግሳችሁ ጠብቁን የሚል ፕሮፓጋንዳ ቢነዛም ህዝቡ አይደናገርም ፡፡” ብለዋል።