ቆቦ ላይ የተቆረጠው ሕወሓት ሃራንም አጣ | አሁን ሎጂስቲክ ከመቀሌ ማምጣት የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል | ሕወሓት በበርሐ ስላሴ ሚኒሻዎች ላይ ዲሽቃ ሲወረውር ዋለ

የሰሜን ወሎ አርሶ አደር ታጣቂዎች በተለይም የድሬ ሮቃና ሶድማ አርሶ አደር ታጣቂዎች በጀግንነት እየተዋጎ የሕወሓትን ኃይል እየመቱ መሆኑን በትናንትናው ዕለታዊ ዜና መዘገባችን አይዘነጋም። እነዚህ አርሶ አደሮች ልክ እንደቆቦና ዞብል ሁሉ ሃራ ላይ የነበረውን የሕወሓት ኃይል ደም ሰሰው ከተማዋን በቁጥጥራቸው ስር ማስገባታቸውን የዘ-ሐበሻ ምንጭ ገልጹ።

ከዞብል የተነሱ አርሶ አደሮች የኢትዮጵያ አየር ኃይል በቆቦ የነበሩትን 9 የሕወሃት ካምፖች በድሮን ካወደመና በርካታዎችን ከደመሰሰ በሁላ ወደ ከተማው በመግባት የተራረፈውን በመጠራረግ ቆቦን በ እጃቸው ማስገባታቸው ይታወቃል። ቆቦ በነዚህ ታጣቂዎች እጅ ከወደቀች በኋላ ሕወሓት ሎጂስቲክስ ከመቀሌ በዚህ መስመር ማስገባት አልቻለም የሚሉት ምንጩ አሁን አልመሃል ላይ ዘርፈው አጠራቅመው የነበረውን ሎጂስቲክ ነው ወደ ሌላ ቦታ የሚያዘዋውሩት ብለዋል።

በተጨማሪም በኮረም በሰቆጣና ላሊበላ መስመርም የአካባቢው ሚሊሻዎች ስለተነሱባቸው ምንም መንቀስቀስ አልቻሉም ያሉት ምንጩ ሕወሓት ወደፊት ከመግፋና ከፊት ለፊትም ከመመታት ውጭ ወደ ኋላ ወደ መቀሌ መመለስ አይችልም ብለዋል።

ለዚህም ይመስላል ሕወሓት የተራረፈ ኃይሉን በሰሜን ሸዋ አካባቢዎች በመሰብሰብ ወደ ፊት ብቻ እየገፋ የሚገኘው የሚሉት ምንጩ በዛሬው ዕለት አርሶ አምባር በተባለ አካባቢና በርሐሥላሴ በተባለ አካባቢ ሚኒሻዎች ላይ መድፍ ሲተኩስ ውሏል። በዚህ አካባቢ ሚንሻው አንድ ብቻ ብሬን ይዞ ሲዋጋ የዋለ ቢሆንም ሕወሓት ዲሽቃ ብቻ በብዛት እየተኮሰ ሚኒሻው የያዘውን ቦታ ከበርሃ ሥላሴ መልቀቁን ምንጩ ተናግረዋል።

ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ የሰሜን ሸዋ ሚኒሻ ከአማራ ልዩ ኃይልም ሆነ ከመከላከያው ከፍተኛ ድጋፍ ሊደረግለት እንደሚገባ ሲያሳስብ ቆይቷል። ሕወሓት በአሁኑ ሰዓት ኃይሉ የተመናመነ ቢሆንም ዲሽቃ በመተኮስ፤ ያልተመጣጠነ ትጥቅ የያዙ ሚኒሻዎችን ቦታ ያስለቅቃል። በመሆኑም በሰሜን ሸዋ አካባቢ ከፍተኛ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ ነው የአካባቢው ምንጮች የሚናገሩት።

ሕወሓት በሰሜን ሸዋ አጣዬ እና ማጀቴ በገባባቸው ቦታዎች ባለሃብቶችን፣ እንዲሁም ሊዋጉ ይችላሉ ያላቸውን ከቤት እያወጣ መግደሉን የሚናገሩት ምንጮቹ፤ በተለይም በአጣዬ አካባቢ ቤት ለቤት እየዞሩ ትጥቅ ለማስፈታት እንደሚሞክሩ መረጃዎች ደርሰውናል።

ከቆቦ የተቆረጠውና ወደ መቀሌ መመለስ የማይችለው ይህ ኃይል ያለው አማራጭ ይህ የሰሜን ሸዋ መስመር በመሆኑ፤ ወደተለያዩ የሰሜን ሸዋ ከተሞች በቀጥታ በመኪና መንገድ አይጓዝም። የአካባቢውን ማህበረሰብ አለባበስ በመልበስ በተራሮች ጭምር አቆራርጦ ወደ አንድ ከተማ በመግባት ግድያዎችን በመፈጸም ከተማው ውስጥ ገባሁ በሚል ያሸብራል። ስለዚህም ከባድ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፤ ዋናው መንገድ ብቻ ሳይሆን የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ሊፈተሹ ይገባል ተብሏል።