በየከተማው የተሰገሰጉ የሕወሓት ትራፊዎች በትግራይ 3 ከተሞች የጠሩት አመጽ ከሸፈ | ከእስር ቤት በሕወሓት ተለቀው ሆን ተብሎ በተሰጠ ሴራ ከሰሜን ዕዝ የተዘረፈውን ዩኒፎርም ለብሰው ሴቶችን አስገድደው ሲደፍሩ የነበሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ

በትግራይ ክልል ሶስት ከተሞች በየከተማው በሕዝብ ውስጥ በተሰገሰጉ የሕወሓት አፍቃሪዎች የተጠራው አመጽ በቁጥጥር ስር መዋሉን የመከላከያ ምንጭ ለዘ-ሐበሻ ገለጹ። በአዲግራት፣ በመቀሌ እና በውቅሮ ከተሞች የተደራጁ የሕወሓት ሰዎች ለአመጽ ወጥተው መሰረተ ለማቶችን ማለትም መብራት እና የስልክ መስመሮችን ለመቁረጥ ሙከራ ሲያደርጉ፤ እንዲሁም የሕዝቡን ሰላም እያስከበረ ባለው መከላከያ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከሩት ላይ እርምጃ ተወስዶ የተገደሉ እንዳሉም ምንጮች ገልጸዋል።

በመቀሌ ከተማ ላለፉት 3 ቀናት የሥራ ማቆም አድማ በሚል የንገድ ቤቶች ተዘጋግተው መቆየታቸውን መዘገባችን የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለት ሁሉም ወደ ሥራቸው መመለሳቸውና ሱቆች መከፋፈታቸውን ሰምተናል።