3 አጫጭር ዜናዎች

 

በሰሜን ጎንደር ግንባር ከፍተኛ ሽንፈትን የተከናነበው አሸባሪውና ደም መጣጩ ምግበ ኃይለ የሚመራው የሕወሃት ኃይል ሽንፈቱን ለማካካስ ትናንት ምሽት ወደ ደባርቅ መስመር መድፍ ከርቀት ሆኖ መተኮሱን የዘ-ሐበሻ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል። እቅዱ ሰላማዊ ሰዎችን ለመምታትና ለመረበሽ ቢሆንም በዚህ ሰሜን ጎንደር ግንባር ከ16 ሺህ በላይ የሕወሓት ታጣቂን የረፈረፉት የሰሜን ጀግኖች ተክሱን ከቁብ እንዳልቆጠሩት ተገልጿል። ሕወሓት የተኮሳቸው መድፎች ምንም ኢላማቸውን ሳይመቱ የገበሬ እርሻ ውስጥ ወድቀዋል።

—–
ቆርቄና ቆሰሉ በተባሉ አካባቢዎች የአካባቢውን ማህበረሰብ በመሳሰል ቆርጠው በመግባት ወደ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ እየተንቀሳቀሱ የነበሩ 43 የሕወሓት ታጣቂዎች በኢትዮጵያ ኃይሎች ተደመሰሱ። ጌታቸው ረዳ እነዚህን ታጣቂዎቹን ተማምኖ ኮምቦልቻ አየር ማረፊያ ላይ የሕዝብ ማመላለሻም የወታደሩም አውሮፕላኖች በዚያ ዝር እንዳይሉ ማስጠንቀቂያ ለጥፎ የነበረ ቢሆንም እነዚህ በቆርቄና ቆሰሉ የመጡ ታጣቂዎች 43ቱም ተደም ሰሰው አስከሬናቸው በየቦታው ተንጠባጥቧል።

—-

ሕወሓት በኩታበር ተሁለደሬ ወደ አምባሰል መውጫ የሚጠቀምበት መንገድ ላይ የሚገኙት ማርያም ዱር እና ዋሻ ጊዮርጊስ ላይ የሚገኙ ኃይሎቹ በዛሪው ዕለት ድንገት በአየር በደረሰባቸው ድብደባ መዛባታቸው ተሰማ። በማርያም ዱርም ሆነ በዋሻ ጎርጊስ ገብቶ የነበረው ኃይል ሲመታ የቀረው በመበታተን የተዛባ ሲሆን በኩታበር ተሁለደሬ ወደ አምባሰል መውጫ የሚጠቀምበት መንገድ መመታቱ በዚያ አካባቢ ያለውን የሕወሓት ኃይልን እንዳፍረከረ ምንጮች ነግረውናል።