የነጌታቸው ረዳ የአማራ ክልል ወጣቶችን አነቃቅቷል | በርካታ ወጣቶች እየዘመቱ ነው

 

ከሰሞኑ የጁንታው ኃይል አመራሮች የሆኑት ጌታቸው ረዳ፣ ጻድቃን ገብረትንሳኤ፣ ጀነራል ታደሰ ወረደ እና ሌሎች የነርሱ ደጋፊ የሆኑ ሚዲያዎች ዋነኛ ጠላታችን የአማራ ሕዝብ ነው ብለው ማስቀመጣቸውን ተከትሎ እንዲሁም የአማራ ክልልን እንወጋለን ሲል ጌታቸው ረዳ ከተናገረ በኋላ በአማራ ክልል ወደ መከላከያው እና ወደ ክልሉ ልዩ ኃይል የሚገባው ሰው ቁጥር እየጨመረ መሆኑ ተነገረ።

በትናንው ዕለት ብቻ ከደብረማርቆስ እና አካባቢው በርካታ ቁጥር ያለው ሕዝብ የዘመተ ሲሆን በአደባባይም ሕዝብ በመውጣት የደስታ ተኩስ በመተኮስ ጭምር አሸኛኘት አድርጓል። በወሎም በሰሜን ሸዋም በጎንደርም ተምሳሳይ ሆኔታዎች እንዳሉ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ተናግረዋል።

በጎንደር የሚገኘው የዘ-ሐበሻ ተባባሪ ዘጋቢ በተለያዩ የምዝገባ ጣቢያዎች በመዘዋወር የተመለከተው ከዚህ ቀደም ታይቶ የማይታወቅ ቁጥር ያለው ሰው ሕዝብ እየዘመተ መሆኑን ነው። መሳሪያ እንደያዙ ለመዝመት የሚመዘገቡ ሰዎችንም አይቻለሁ ያለው ዘጋቢው የሕዝቡን ስሜት ያስነሳው የጌታቸው ረዳ ንግግር እንደሆነ እንደተረዳ ገልጿል።

በአማራ ክልል በኩል እየተቀየሩ ያሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሲያልፉ ሕዝቡ በከፍተኛ ሁኔታ እየተቀበለ ደጀንነቱን እየገለጸ መሆኑን በትናንትናው የዘ-ሐበሻ ዜና ዘግበናል።

በሌላ በኩል ትግራይ ተወላጆች የሚዘጋጀው ግ ዕዝ ሚዲያ፤ ጁንታው የትግራይ ህዝብ እንዳያስፈጅ ያሰጋል ሲልያለውን ስጋት አስቀምጧል። ጁንታው ትላንት ለመደራደር 7 ነገጥቦች ብለው ያወጡት መግለጫ ለመደራደር ሆነ ቶክስ ለማቆም እንደማይፈልጉ ነው ከነጥቦቹ መረዳት የሚቻለው።
ጁንታው ወደ ኤርትራ መተኮሱ አይቀርም በጣም የሚያሰጋው ነገር የኤርትራ ጦር ለዚህ መልስ መስጠቱ አይቀርም እና ትግራይ እንዳይደመስሳት በጣም ያሰጋል። ምክንያቱም ጁንታው መካናይዝድ ሃይል የለውም ነገር ግን የኤርትራ ጦር መካናይዝድ ሃይል ያለው ፕሮፌሽናል አርሚ ነው። እዚ ላይ ሊሰመርበት የሚገባ የኤርትራ ጦር ምንም ምህረት እንደሌለው የትግራይ ህዝብ ላለፉት ስድስት ወራት በተግባር አይቷል።
ጁንታው ትላንት በእልህ ለራሳቸው ኢጎ ሲሉ የትግራይ ህዝብ ወደ መከራ አስገብተው አሁን ደሞ ጠቅልለው የትግራይ ህዝብ እንዳያስፈጁ ያሰጋል። ጁንታው እኔ የማልመራት ሃገር ትጥፋ የሚል የዶሮ አስተሳሰብ ነው ያለው።
ጁንታው ከሰሜን እዝ ይሄ ሁሉ ጦር መሳርያ ቀምቶ በሁለት ሳምንት ተሸንፏል አሁን በተዳከመ ሃይሉ ከማንም ጋር ፀብ ከጫረ የትግራይ ህዝብ ማስፈጀቱ አይቀሬ ነው። ሲል በጽሁፍ ስጋቱን ገልጿል።