ኢትዮጵያውያን ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ ዛሬ በትዊተር ዘመቻ ከፈቱ

የዓለም ጤና ድርጅት ስልጣኑን ተጠቅሞ ለሚያገኛቸው የሃገር መሪዎች እና ተቁዋማት ሃሰተኛ መረጃ በመስጠት ሕወሃትን ከወደቀበት ለማንሳት የዲፕሎማሲ ሥራ እየሰራ በሚገኘው ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በትዊተር ዘመቻ ከፈቱ።

በመንግስት ባለስልጣናት ድክመት በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ቆንስላ ዲፕልማቶች ድክመት በአሁኑ ወቅት ሕወሓት በውጭ ሃገር የበላይነቱን በመያዝ ከሚጠጣው እና ከሚበላው እያካፈለ የትግራይ ሕዝብን ደህንነት እየጠበቀ የሚገኘው ጀግናው ኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስም በደፋሪነትና በቀማኛነት ስሙ በሃሰት እየጠፋ ይገኛል። ከቤኒሻንጉል፣ ከኦሮሚያ፣ ከኮንሶ፣ ከጉራ ፈርዳና ከሌሎችም አካባቢ የተፈናቀሉ ሕዝቦች በላይ ለትግራይ ሕዝብ ከፍተኛ እርዳታ መንግስት እያቀረበ ቢሆንም እነቴዎድሮስ አድሃኖም በዲፕሎማሲው መስክ በኢትዮጵያ መንግስት ላይ ብልጫውን መውሰዱ ያንገገባቸው ኢትዮጵያን ቴዎድሮስ አድሃኖምን ሴራ የሚያጋልጥ፣ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን የገደለውን ሕወሓትን ለማዳን እየሰራ እንደሆነ፣ ሰራዊቱ ሕግን እያስከበረና ከሚበላውና ከሚጠጣው ጭምር ለትግራይ ሕዝብ እያካፈለ እንደሆነ፣ ቴድሮስ ከተሾመበት የዓለም ጠና ድርጅት ስራው ይልቅ የሕወሓት ጉዳይ ፈጻሚ መሆኑን እና ሌሎችን የሚገልጹ የትዊተር ዘመቻዎች ዛሬ እያካሄዱ ነው።

በመንግስት እንዝላልነት፤ በዲፕሎማቶች ስንፍና ግድ የለሽነት እንዲሁም የሕወሃት ተላላኪነት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብና ሕይወቱን ለሃገሩ አሳልፎ የሰጠው የመከላከያ ሰራዊቱ ስም መጥፋት የለበትም የሚሉት ኢትዮጵያውያኑ፤ ኢትዮጵያውያን መንግስትን ሳይጠብቁ ወደ ትዊተር በመሄድ ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቡዋል።

በአሁኑ ሰዓት እነ ቴዎድሮስ እያሰራጩት ባለው ሃሰተኛ የዲፕሎማሲ ዘመቻ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ ከፍተኛ ጫና እንዳደረ እየተነገረ ነው።

https://risingethio.com/2021/02/04/dr-tedros-is-responsible-for-the-misinformation/?fbclid=IwAR3i5Wpch9C15qjN3-bzmtw2DAKTM2DDcXkVZkYqECNKxPXW_-UnQ3Rw5FM