የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በሚላኖ እና አካባቢዋ ወቅታዊ መግለጫ

#ጉዳዩ  በሚላኖ ስለሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ፈለገ ሠላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ይሆናል። 

  ኮሚኒቲዉ ይህንን  መግለጫ  ሲያወጣ  ሃይማኖት  እና ፖለቲካ  የተለያዩ  መሆናቸውን  በጽኑ ያምናል ይህንንም  በማክበር ለሀገር እና ለሕዝቦች ዲሞክራሲያዊ እና መከባበር ይታገላል ይህንንም  መሰርት  ባደርገ መልኩ  ከዚህ  በፊት  በሃገራችን  ውስጥ የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ ሃይማኖትን  እና ዘርን  መሰረት  ባደረገ መልኩ በአሰቃቂ በሆነ መንገድ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው እጅግ ዝግናኝ ግድያ፣የአካል መጉደል፣የመፈናቀል እና የንብረት መውደም

   በደረሰበት   ወቅት በሚላኖ  የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ   በቀን 25/07/2020 መንግስት የህዝቦችን ሰላም  እንዲያስጠብቅ እና ሕግን  እንዲያስከብር በተጠራው   ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የቤተ ክሪሲቲያኒቱ ካህናት በመገኘት ለሞቱት ወገኖቻችን  ጸሎተ ፍትሃትና በስልፉ ላይ ለተገኙትም ሕዝብ የመጽናናት መልእክት እንዲያስተላልፉ በኮሚኒቲው በኩል ደብዳቤ ተልኮላቸው ምንም አይነት መልስ ሳይሰጡ በመዘግየታቸው  እንደገናም በእጅ ስልካቸው ላይ ብንደውልም መገኘት እንደማይችሉ በወቅቱ ምላሽ በመስጠት ሳይገኙ ቀርተዋል

 ዛሬ ግን የትኛውንም ሕዝብ የማይወክሉ ለአመታት ሃገርን እየመዘበሩ እያወደሙ ሕዝብን እያገላቱ  ለሕግ  አልገዛም  ብለው የሃገርን  ልዕልና ተዳፈርው በመርጡት  መንገድ እርምጃ  ለተወሰደባቸዉ   የእናት  ጡት ነካሾች ለሆኑ የጥፋት ኀይል ለሆኑት የጁንታው አባላት አጋር በመሆን  የቅድስት ቤተ ክርስትያን ካህናት እና አገልጋዮች ቆመው ማየታችን ትልቅ ታሪክና ትውፊት ያላትን ቅድስት ቤተ  ክርስቲያን በጥቂት ለጥቅማቸው እና ለዘራቸው በቆሙ አገልጋዮች ነን ባዮች እንዲህ በዚህ ደረጃ ወርዳ ስናይ የተሰማን ጥልቅ ሃዘን በቃላት የሚገለጽ አይደለም። 

  ስለሆነም  ለእምነቱ ተከታዮች ምእመናን እና ለሚመለከተው አካል  በሙሉ ሃዘናችንን ለማሳዎቅ  እንወዳለን

   ከአክብሮት  ሰላምታ  ጋር

      የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ በሚላኖ