87 የሕወሓት ትርፍራፊ ወታደሮች በራያ አካባቢ በተደረገ ውጊያ ተደመሰሱ | ረሃቡ የጠናባቸውና በውጊያው የተሸነፉ የትህነግ ወታደሮች ለአማራ ልዩ ኃይል እጅ ሰጡ

(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአለፉት 4 ቀናት ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እስከ አሁኑ ሰዓት ድረስ የሕወሓት ኃይል በርሃብ በሎጂስቲክ እጥረት ከማልቅ በሚል ሰብሮ ለመውጣት የሞት ሽረት ትግል እያደረገ መሆኑን በጠዋቱ 3 ልዩ መረጃዎች ሪፖርት ማቅረባችን ይታወሳል።  በተለም በነጀነራል አሰፋ ቸኮል በመከላከያው ተከቦ ገፍቶ እየመጣበት በመሆኑ መፈናፈኛ ያጣውና ከፍተኛ ውድመት የደረስበት የሕወሃት ኃይል ከትናንት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ በኮረም አቅጣጫ ሰብሮ ለመውጣት በስፍራው ከሚገኘው ከአማራ ልዩ ኃይል ጋር ውጊያ እንደገጠመ ምንጩ ተናግረዋል። በኮረም አቅጣጫ ሰብሮ ለምውታት እየታገለ የሚገኘው የሕወሃት ኃይል ክፉኛ ተደምሦሶ የቀረው ኃይል ወደ ኋላ መለሱን ዘግበን ነበር።

አሁን በደረሰን ተጨማሪ መረጃ  ዛሬ መጋቢት 4/2013  ዓ.ም ንጋት አከባቢ  ጀግናው የአማራ  ልዩ ሀይል በዋግህምራ  እና በራያ አዋሳኝ በሚገኘው  ተከዜ በርሃ ውስጥ  ተቆርጦ  የቀረው የጁንታውን ቅሬታ አካል ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገልጸዋል። 

የአማራ ልዩ ሐይል በሎጀስቲክ አቅርቦት የተዳከመውን የጁንታው ቅሪት ሐይል ላይ በወሰደው እርምጃ እስካሁን በተቆጠረ አስከሬን 8 አባላቱ  ተደምስ ሰዋል፤ በተጨማሪም በአብዛኞቹ ደግሞ እጅ ሰጥተዋል ሲሉ አንድ ስማቸው እንዳይገለጽ የፈለጉ የጦር መኮንን ነግረውኛል። 

ይሁን እንጂ ስለ ጉዳዩ በአማራ ክልል መንግስት በኩል ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የተባለ ነገር የለም። ይሁን እንጂ የአማራ ክልል መንግስ የክልሉ ልዩ ሐይል የሰራውን ጀብድ ለክልሉ ይፋ ማድረግ፤ የተማረኩትንም በቴሌቭዥን አቅርቦ ማሳየት እንደሚጠበቅበት የተለያዩ ኃይሎች እየጠየቁ ነው።