በደቡብ ሱዳን የሰላ ማስከበር ግዳጃቸውን የፈጸሙ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በአየር ማረፊያ ውስጥ ረብሻ ፈጠሩ | ጥገኝነት ይሰጠን እያሉ ነው | ሁለት የሻለቃ ማዕረግ ያላቸው የትግራይ ተወላጅ የሰራዊቱ አባላት ከዱ

በደቡብ ሱዳን በሰላም ማስከበር ግዳጅ ላይ የነበሩ እና ግዳጃቸውን ጨርሰው ለመመለስ በጁባ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ላይ የነበሩ የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ረብሻ መፍጠራቸውና አንዳንዶቹም ጉዳት እንደደረሰባቸው የዘ-ሐበሻ የመከላከያ ምንጭ አስታወቁ።

ምንጩ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት “የዛሬው ጉዞ ዋና አላማ ግዳጃቸውን የጨረሱት የ12ኛ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ወደ ሃገር ቤት የሚመለሱበት እና ተተኪያቸው የሆኑት የ15ኛ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚገቡበት፤ የሚቀያየሩበት በረራ ነበር። በዚህ ወቅት የትግራይ ተወአጅ የሆኑ ግዳጃቸውን የጨረሱ የ12ኛ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት የሆኑ የመከላከያው አባላት ወደ ሃገር ቤት አንመለስም በሚል በሚል በአየር ማረፊያው ውስጥ ብጥብጥ ለማስነሳት ሞክረዋል።

ባሳለፍነው ቅዳሜ ሁለት የሻለቃዋ አባላት በዛው በጁባ ደቡብ ሱዳን መክዳታቸውን የገለጹት የዘ-ሐበሻ ምንጭ አንደኛው በሰሜን እዝ ሆስፒታል ፐርሶኔል ሃላፊ የነበረ እና ሁለተኛው ደሞ በዛው በሰሜን እዝ ሚሳኤል ምድብ ላይ ይሰሩ የነበሩ ናቸው ብለውናል። 

በጥቅምት 24ቱ ጥቃት እጃቸው እንዳለበት የሚጠረጠሩት እነዚሁ የሻለቃ አባላት ጥገኝነት ጠይቀዋል። እነዚህ ሁለት ሻለቃዎች የሚመሩት የሻለቃው ጦር በአጠቃላይ 850 አባላት የነበሩት ቢሆንም የከዱትን 2 ሻለቃዎች ወደ ሃገር ውስጥ ለመመለስ ምን እየተሰራ እንደሆነ አልታወቀም። 

ዛሬ በጁባ አየር ማረፊያ ወደሃገር ቤት አንመለስም በማለት ረብሻ ያስነሱት እነዚህ ወታደሮች ወደ ሀገር ቤት አንመለስም ጥገኝነት ይሰጠን የሚል ጥያቄ ሲያቀርቡ ነበር። በአየር ማረፊያው ውስጥም  ከፍተኛ ወከባ፣ ጩኸት፣ መሬት ላይ መንከባለል እና የመሳሰሉትን ፈፅመዋል።

እነዚሁ የ12ኛ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ አባላት የሆኑት የትግራይ ተወላጅ ወታደሮች አብዛኞቹ ሀገር ቤት በተፈጠረው ችግር በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፎ የነበራቸው በመሆኑ ሀገር ቤት እንደደረስን እንታሰራለን የሚል ስጋት ሊሆን እንደሚችል  ይገመታል የምሉት ምንጩ በዚህ ግርግር ውስጥ የዩናሚስ ዋና የሃይል አዛዥ የሆነው ህንዳዊው ሌተናል ጄነራል ሻሊሽ ቲናካር እጁ እንዳለበት ይገመታል ይላሉ።

እነዚህ የትግራይ ተወላጅ የሆኑት ወታደሮች ዓላማቸውየሀገርን ገፅታ ማበላሸት ነው። በሰው ሃገር ላይ መሳቂያ ሊያደርጉን ቢሞክሩም ለሎች የሰራዊቱ አባላት እርምጃ በመውሰድ እንዲረጋጉ እንዳደረጓቸው ተሰምቷል።

እስካሁን ድረስ ወደ ኢትዮጵያ አንመለስም  ያሉትን ወደ 15 የሚጠጉ የትግራይ ተወላጅ የሰራዎት አባላት የተመድ ሰብአዊ መብት ክፍል ልዩ ከለላ በመስጠት በኤርፖርቱ ውስጥ በሚገኝ አንድ ክፍል ውስጥ ዘግተውባቸው እንደሚገኙ የገለጹት ምንጩ እጣፈንጣቸው እንዳልታወቀ ገልጸውልናል።

የዛሬው የሃይል ቅያሪ በረራ የመጀመሪያ ሲሆን ከዚህ በኋላ በቀጣይ ጊዜያት የሚደረጉ 4 ቀሪ በበራዎች በመኖራቸው ምን እንደሚፈጠር አናውቅም የሚሉት የዘ-ሐበሻ ምንጭ፤

ምንም እንኳን ከመከላከያ ሰራዊቱ፤ እነዚህ የትግራይ ተወላጅ ወታደሮች ይህን ሊፈጥሩ እንደሚችሉ መረጃው ከደረሰን ቀናት ቢያልፉም፤  በተመድ በኩል የካሜራ ሞያተኞች ፣ የሰብአዊ መብት ክፍል እና የመሳሰሉት በተጠንቀቅ በአየር ማረፊያው ላይ ይገኙ ነበር ብለዋል።  ለመረበሽ የሞከሩትን አባላት ለብቻ ወደተዘጋጀላቸው ክፍል ያስገቧቸው ሲሆን የተቀሩት ሰላም አስከባሪ አባላት ወደ ኢትዮጵያ ጉዞአቸውን እንዲቀጥሉ ትእዛዝ ተሰጥቷል ሲሉ ምንጩ ጉዳዩን ተከታትለው እንደሚነገሩን በመግለጽ የዛሬውን ውሎ ነግረውናል።