“ጤፍ ለምን በመላው አለም ምርጥ እህል ሆኖ ተወዳጅ ሆነ?”

ኤንዲ ቲቪ በምግብ አምዱ ላይ ዛሬ ‹‹ጤፍ ለምን በመላው አለም ምርጥ እህል ሆኖ ተወዳጅ ሆነ?›› ሲል በጥያቄ ዘገባውን ጀምሯል፡፡ ሲቀጥልም ከጥንታዊ እህል ዘሮች ሁሉ በጣም ጥቃቅን የሆነው ጤፍ እስካሁን ያልተዘመረለት ትልቅ ሚስጢር እንዳለው አስታውቋል፡፡ 

በኢትዮጵያዊያን ሯጮችና አትሌቶች በሚስጥር ተይዞ የቆየው ይህ እህል አሁን በመላው አለም ተጠቃሚው በከፍተኛ መጠን መጨመሩንም አስረድቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ጤፍ በአሜሪካ፣ በካናዳ፣ በአውስትራሊያ፣ በስዊዘርላንድና ኔዘርላንድስ በስፋት መዘራትና መታጨድ እንደጀመረም ገልጿል፡፡

የጤፍን የጤና ጠቀሜታዎች የዘረዘረው ዘገባው በካልሺየም፣ ኮፐርና ዚንክ ይዘቱ ከስንዴ፣ ማሽላና በቆሎ የበለጠ እንደሆነም አስታውቋል፡፡ ጤፍን እንዴት አዘጋጅቶ መመገብ እንደሚቻልም በዘገባው ላይ በምሳሌዎች አቅርቦ አይተናል፡፡