Archive

Category: News

የኢዜማ ፓርቲ የቢሾፍቱ ከተማ የአድአ ምርጫ ወረዳ 1 ሊቀመንበር ተገደሉ

በግንቦት ወር መጨረሻና በሰኔ ወር መጀመሪያ ከትግራይ ክልል ውጪ በመላው ኢትዮጵያ ለማካሄድ በታቀደው 6ኛው አገራዊ ምርጫ 52 የፖለቲካ ፓርቲዎች እንደሚሳተፉ ይጠበቃል። ከነዚህ ፓርቲዎች መካከል ኢዜማ አንዱ ነው። ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት የፓርቲዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ ጀምሯል። በቢሾፍቱ ከተማ የምረጡኝ ቅስቀሳ ለመጀመር አንድ ቀን ሲቀረው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ…

የኢትዮጵያ መንግስት ሎቢ የሚያደርግ ድርጅት መቅጠሩ ተሰማ፡

ኢትዮጵያ የገጠማትን የዲፕሎማሲ ቀውስ ለመመከት በአሜሪካ ኮንግረስና በጆ ባይደን አስተዳደር ሎቢ የሚያደርግ ድርጅት መቅጠሯን ፍርይን ሎቢ ዘግቧል፡፡ እንደዘገባው የተቀጠረው ‹‹ቬናብል›› የሚባል በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኝ የህግ ተቋም ነው፡፡ በዋሽንግተን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከድርጅቱ ጋር በወር ሰላሳ አምስት ሺህ ዶላር ለመክፈል ስምምነት መፈፀሙም ተዘግቧል፡፡ በስምምነቱ መሰረት ውሉ ከፌብሩዋሪ አንድ ቀን ጀምሮ የሚፀና…

በትግራይ ም ዕራብ ሽሬ አካባቢ ተኩስ የከፈተው የሕወሓት ኃይል በ20 ደቂቃ ውስጥ ተደመሰሰ

ለረዥም ጊዜ በተከዜ በረሃ መሽጎ እጅ አልሰጥም ያለው የሕውሓት ሰራዊት ሙሉ በሙሉ ከተደመሰሰ በኋላ  በትግራይ ጦርነት የሚባል ነገር የለም ሲሉ አንድ የመከላከያ ምንጭ ለዘ-ሐበሻ ገለጹ። የመከላከያው ምንጭ ሕወሓት ሲተመንበት የነበረው የተከዜው በረሃ ጦር ከተወገደበት በኋላ አሁን በየአካባቢው ተበታትኖ የቀረ ሰራዊት ነው ያለው ብለዋል። Shire Map በየስፍራው ተበታትኖ ያለው የሕወሓት ኃይል…

“ጤፍ ለምን በመላው አለም ምርጥ እህል ሆኖ ተወዳጅ ሆነ?”

ኤንዲ ቲቪ በምግብ አምዱ ላይ ዛሬ ‹‹ጤፍ ለምን በመላው አለም ምርጥ እህል ሆኖ ተወዳጅ ሆነ?›› ሲል በጥያቄ ዘገባውን ጀምሯል፡፡ ሲቀጥልም ከጥንታዊ እህል ዘሮች ሁሉ በጣም ጥቃቅን የሆነው ጤፍ እስካሁን ያልተዘመረለት ትልቅ ሚስጢር እንዳለው አስታውቋል፡፡  በኢትዮጵያዊያን ሯጮችና አትሌቶች በሚስጥር ተይዞ የቆየው ይህ እህል አሁን በመላው አለም ተጠቃሚው በከፍተኛ መጠን መጨመሩንም አስረድቷል፡፡…

የችሎት ዜና

ጠቅላይ  ፍ/ቤቱ  ምስክር  እንዳይሰማ  ሲል  የእግድ  ትዕዛዝ  ሰጠ። ልደታ  ፍ/ቤት  ጥር  5/2013ዓ.ም. በዋለው ችሎት አቃቢ ሕግ ለዛሬ በባልደራስ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ምስክሮችን ማሰማት እንዲጀመር መቅጠሩ ይታወሳል። ይሁን  እንጅ  ችሎቱ ምስክር መስማት አልቻለም። አቃቤ ሕግ ከጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ቸሎት  ምስክር እንዳይሰማ ትዕዛዝ አምጥቻለሁ በማለቱ ምስክሮች ሳይቀርቡና ሳይደመጡ ቀርተዋል። ጉዳዬ በጠቅላይ…

የትግራይ መከላከያ ቃል አቀባይ ነኝ የሚለው ገብረ ገብረጻድቅ አገኘነው ያለው 3 የድል ዜና ሕልም አይከለከልም የሕወሓት ምላስም አይሞትም የሚለውን የሚያስታውስ ነው ተባለ

ራሱን የትግራይ መከላከያ ኃይል ቃል አቀባይ ነኝ የሚለው ኃይል ገብረ ገብረጻድቅ ዛሬ በድምጺ ወያኔ በድምጽ ተቀርጾ ባስተላለፈው መል ዕክት የትግራይ መከላከያ ሰራዊት ከአክሱም ወደ አዴት ሲጓዝ የነበረ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት አንድ ሻለቃ ጦርን ሕደግ ውረድ የተባለ አከባቢ ሙሉ በሙሉ ደመሰስኩ የሚልና ተጨማሪ የድል ዜናዎች በሚል ያሰራጨው መረጃ ፍጹም ሃሰት እንደሆነና…

ትራፊው የሕወሃት ጁንታ የመቀሌን ሕዝብ ለአመጽ ለማነሳሳት መብራት ቆረጠ

የሃውዜን ጭፍጨፋ ልምድ ያለው ሕወሓት በትራፊ ተላላኪዎቹ አማካኝነት በመቀሌ ከተማ የተለያዩ ሳቦታጆችን እየፈጸመ እንደሆነ ተሰማ። ትናንት ለሶስት ቀናት የሚል የቤት ውስጥ አድማ እንዲጠራ ያደረገው ትራፊው ቡድን ዛሬ ደግሞ ሆን ተብሎ የመብራት መስመር ቆርጧል። ከዚህ ቀደም ጦርነቱ በተጀመረ ግዜ ሕወሃት የስልክ እና የመብራት መስመሮችን ቆራርጦ ህዝቡን በጨለማ ውስጥ ከጣለው በኋላ ውጫ…

ተቆርጦ የቀረ የሕወሓት ጦር በሁለት አካባቢዎች መደምሰሱ ተሰማ

ከቆላ ተንቤን በረሃ ከትሞ የነበረው የሕወሓት ጦር በ4 ቀን ጦርነት ከተደመሰሰ በኋላ አሁን ደግሞ በሌሎች የትግራይ ገጠር አካባቢዎች ተቆራጠው የቀሩትን የሕወሓት ጦር አባላት የማሳደዱና የመደምሰሱ ሥራ እንደቀጠለ መሆኑን የዘ-ሐበሻ የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል። ከአክሱም ወደ ሽሬ በሚያስኬደው መንገድ አካባቢ በምትገኝ አፍጋህጋ በተባለች አካባቢ ተራራ ውስጥ ከትሞ የከረመው የሕወሓት ጦር በአካባቢው ነዋሪ…

በመለስ ዜናዊ አካዳሚ ስም በአዲስ አበባ የተሰራው ህንጻ ሆስፒታል ሊሆን ነው

ከጅጅጋ እስከ ባህርዳር፤ ከአፋር እስከ ወለጋ፤ ከጎንደር እስከ ቀብሪዳር፤ ከጋምቤላ እስከ ቤኒሻንጉል፤ ከደብረማርቆስ እስከ ሐረር በመለስ ዜናዊ ስም የተሰየሙ ፓርኮች፣ ትምህርት ቤቶች፣ ሆስፒታሎች እና ወዘተ ስማቸው ላለፉት 3 ዓመታት እየተፋቀ በሌላ ሲቀየሩ ቢቆይም በአዲስ አበባ በመለስ ዜናዊ ስም ያሉ ነገሮች ሳይነኩ ቆይተዋል። አሁን ግን ጊዜው እየደረሰ ይመስላል። በአዲስ አበባ በመልስ…

ኢትዮጵያውያን ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ ዛሬ በትዊተር ዘመቻ ከፈቱ

የዓለም ጤና ድርጅት ስልጣኑን ተጠቅሞ ለሚያገኛቸው የሃገር መሪዎች እና ተቁዋማት ሃሰተኛ መረጃ በመስጠት ሕወሃትን ከወደቀበት ለማንሳት የዲፕሎማሲ ሥራ እየሰራ በሚገኘው ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ ኢትዮጵያውያን ዛሬ በትዊተር ዘመቻ ከፈቱ። በመንግስት ባለስልጣናት ድክመት በውጭ ያሉ የኢትዮጵያ ኢምባሲዎች እና ቆንስላ ዲፕልማቶች ድክመት በአሁኑ ወቅት ሕወሓት በውጭ ሃገር የበላይነቱን በመያዝ ከሚጠጣው እና ከሚበላው እያካፈለ…