የባልደራስ የውጭ አማካሪ ምክር ቤት አባላት ማንነት ታወቀ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ የአማካሪ ምክር ቤት አባላት ማንነት በይፋ ታወቀ። በሰሜን አሜሪካ እና አውሮፓ የሚገኙ እነዚህ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፓርቲውን በተለያዩ እስትራቴጂክ እና ፖሊሲ ጉዳዮች ላይ በማማከር ድጋፍ መስጠታቸውንም ለዘሃበሻ የደረሱ መረጃዎች ጨምረው ገልፀዋል።
አንጋፋውን ምሁር ፕሮፌስር ጌታቸው ሃይሌ ፣ዶክተር ሰማሃኝ ጋሹ፣ዶክተር አብርሃም አለሙ፣ አቶ ሃይለገብርኤል አያሌው፣የህግ ባለሙያው ዶክተር ፍፁም አቻም የለህ፣ ዶክተር ኢንጂነር ሉልሰገድ አያሌው፣አቶ ማስተዋል ደስአለው፣ዶክተር ሃምሳሉ አስናቀ፣እና አቶ መስፍን አማንን ያቀፈው የአማካሪ ምክርቤት በመጪው ምርጫ ባልደራስ የአዲስ አበባን ህዝብ የሚጠቅሙ አማራጮችን አቅርቦ እንዲመረጥ ለማድረግ በማገዝ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።