ሕወሓት ደሴን ለመቆጣጠር እየገበረ ያለው ሕዝብ ብዛት የትግራይን እናት ካለ ልጅ የሚያስቀር ነው ተባለ | ጠዋት ላይ ህወሓት ሰርጎ በመግባት ይስማኖ አካባቢ ሚኒሻው ላይ ተኩስ ከፍቶ ነበር | ወዲያው ተጠራርጎ ተደምስሧል የቀረው ወደ አላንሻ ሸሽቷል | ወደ ደሴ 5 ጊዜ መድፍ የጣሉት አስተኳሾች በድሮን ተመተው በእሳት ተጠባብሰው ተደምሰሰዋል

 

አሸባሪውና ወራሪው የሕወሓት ኃይል ደሴን ለመቆጣጠር ዛሬም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የትግራይ ተወላጆችን እየማገደ ነው። ትግራይ በዚህ ዓይነት ከጊዜ በኋላ ወጣት አልባ መሆኗ የማይቀር ከመሆኑም በላይ የትግራይ እናቶችንም ካለ ጧሪ ቀባሪ የሚያስቀር እርምጃ ሕወሓት እየወሰደ ነው። የዘ-ሐበሻ ምንጭ እንደሚሉት ሕወሓት ትናንት ምሽቱን የደሴን ሕዝብ ለማሸበር ከርቀት ከባድ መሳሪያዎችን ተኩሰዋል።

ትናንት ምሽቱን ወደ ደሴ ሕወሓት 5 መድፎችን የተኩሰ ሲሆን ሰኞ ገበያ መስጊድ ጀርባ፣ አይጠየፍ ትምህርት ቤት ጎንና አንድ ራቅ ብሎ እንዲሁም አይጠየፍ ቤተመንግስትና ጎን መድፎቹ ወድቀዋል። እነዚህ ወደ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተተኩሱት መድፎች ሕዝብን በጅምላ ለመግደል የተላኩ ቢሆንም ኢላማቸውን ሳይመቱ ቀርተዋል። የደሴ ሕዝብም የተተኮሰው መድፍ ሳያሸብረው እንደውም አጠንክሮት ለቆራጡ ትግል አዘጋጅቶታል የሚሉት ምንጩ፤ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ድሮኖች ወደ ደሴ ሕዝብ የተተኮሱትን መድፎች በማውደም ትልቅ ሥራ ሰርተዋል ብለዋል።

እንደ ምንጩ ገለጻ መድፉ ወደ ሚተኮስበት ሥፍራ በመሄድ የኢትዮጵያ ድሮኖች መድፎቹን ከነአስተኳሾቹ ያወደሟቸው ሲሆን እስከሬናቸው በ እሳት ተጠባብሶ ሜዳ ላይ ከነመድፎቹ ቀርተዋል ሱሉ ተናግረዋል።

ትናንት ምሽት 5 መድፎችን የጣለው ሕወሓት ዛሬ ጠዋት የተወሰኑ ሚኒሻዎቹን ዛሬ ወደ ደሴ አሰርጎ አስገብቶ ነበር። ከዩኒቨርሲቲው ጥቂት አለፍ ብሎ ይስማኖ አካባቢ ገብተው የነበሩት የሕወሓት ታጣቂዎች በአካባቢው በሚገኙ ሚሊሻዎች ላይ ተኩስ በመክፈት ጉዳት አድርሰዋል። ሆኖም ግን የኢትዮጵያ ኃይሎች ወዲያውኑ በመግባት እነዚህን የሕወሓት ታጣቂዎች ጭጭ ምጭጭ ያደረጓቸው ሲሆን የተራረፈው ኃይል ወደ አላንሻ መሸሹን ምንጩ አክለዋል።

በሌላ በኩልም የወሎ አካባቢ ከፍተኛ አመራሮች Seid Mohammed Hussien እና
Kemal Zeinu “#የክተት ጥሪ ለጀግናው የወሎ ህዝብ በሙሉ፡-” በሚል ጥሪ አድርገዋል።
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
ጀግናው የመከላከያ የምድርና አየር ሃይላችን፡ ልዩ ሃይላችን፡የአማራ ህዝባዊ ሃይሎች(ሚኒሻ፡ ፋኖ ወዘተ) በሙሉ በሚደንቅ ብቃትና ጀግንነት በጁንታው ላይ ከባድ ኪሳራ እያደረሱበት ይገኛል። ጁንታው የትግራይን ህዝብ እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የቀን ሟች እያቀደ ለማፊያው አመራሮች ጥቅም ሲባል ፊዳ እያደረገው ይገኛል።
ሌላው አሳዛኙ ነገር ወያኔ በገፍ ንፁሃን እንድሞቱ እያደረገ ያለው የወሎ ዕምብርት የሆኑትን ደሴና ኮምቦልቻን ለመዝረፍ መሆኑ ነው።
የተወደዳችሁ ወገኖች በጽናት ተዋግተን በሁለትና በሶስት ቀን በሚቋጭ ጦርነት ህዝባችንና ንብረታችንን አትርፈን፡ የህዝባችንን የአሸናፊነት ስነ-ልቦና ገንብተን ለማለፍ እንደህዝብ ተደራጅተን በጀግንነት ይሄን ወራሪና ዘራፊ ሃይል በመመከት ታሪክ ልንሰራ ይገባል።
ማን ለማን ይሸሻል? እስከየትስ ይሸሻል? በጦርነቱ ከቀየው የተሰደደ፡ ሀብት ንብረቱ የተዘረፈ፡ እጁን ለእርዳታ የሚዘረጋ፡ ስነ-ልቦናው የተጎዳ ህዝብ ሊኖረን አይገባም።
ስለሆነም በእስልምና ዕምነት ጅሃድ አውጀን/ በክርስትና ዕምነት ገዝተን ሁላችንም ያለንን የማጥቂያ መሳሪያችንን ይዘን ጠላት ወደ አለበት በመሄድ ፊት ለፊት በመግጠም እንቅስቃሴውን እንግታ፡ እየገደል እንታጠቅ፡ ተዋርዶ ከመኖር-በጀግንነት ተፋልመን ሸሂድነትን ወይም ጽድቀትን እንውረስ!!!
ድል ለህዝባችን!!
_———–

በቦሩ ሜዳ የጠላት ሃይል ይዞት የነበረውን ከሶስት በላይ ምሽጎች በጀግናው የወገን ጦር ተሰባብሯል። ጠላት ይጠቀምባቸው የነበሩ በርካታ ዲሽቃ ስናይፐር ብሬኖች ተማርኳል። የጠላት ሃይልም በከፍተኛ ሁኔታ እንደ ቅጠል ረግፏል።

ደመኛ ጠላት እንደ እህል ከላይ ከላይ ተደራርቦ ተጭኖ ቢመጣም እያራገፍን ወደማዳበርያነት እየቀየርነው እንገኛለን። አሸናፊነታችን የሚያጠራጥር አይደለም። የጠላት ሃይል አሁንም ያለ የሌለ ሃይሉን ተጠቅሞ ደሴንና ኮምቦልቻን በመያዝ ሂሳብ ለማወራረድ ያለው ፍላጎት የተገታ አይደለም። ከጀርባ ተጨማሪ ሃይል መጫን መቀጠሉን መረጃዎች ያመላክታሉ።

ጠላት በሕዝባዊ ማዕበል ወደ ደሴ ሲተም እኛም በተመሳሳይ መንገድ ጁንታውን ለመቅበር በከፍተኛ ወኔና ዝግጅ ልንተም እንጅ ጠላት በሚነዛው የሽብር ወሬ ልንረበሽ አይገባም። ጠላት ከላይ ከላይ ሃይል እያመጣ ሲያራግፍ እኛም ከጠላት ያነሰ ቁጥር ያለን አይደለምና እሱን ማድረግ ይገባል።

የደሴና የአካባቢው ወጣቶች ከወገን ጦር ጎን በመቆም የጀመራችሁትን በማጠናከር ውሃ አቀብሉ። ጥይት ስንቅ በመሸከም አግዙ። በአግላይነት ተሰማሩ። ሰፈራችሁን ከፀጉረ ልውጥ ሰርጎ ገቦች ጠብቁ። ኬላ በመጣል ጠንካራ ፍተሻ አድርጉ። ከደሴና ከአካባቢው የራቀው ወገን ደግሞ በገንዘቡ በቁሳቁስ በሞራል የወገንን ጦር እስከመጨረሻው በማገዝ ጦርነቱን በአንፀባራቂ ድሎች ባጠረ ጊዜ ባነስተኛ መስዋዕትነት እንዲቋጭ ታሪካዊ ኋላፊነታችሁን ለመወጣት የምትችሉትን ሁሉ ጠጠር ወርውሩ።

ይህን ማድረግ የማይችል ሰው ተሸብሮ ባለማሸበር ፈርቶ ባለማስፈራት በጥቅሉ ከአፍራሽና ከወኔ ሰላቢ የወያኔ አጀንዳ ከማሻሻጥ ሊቆጠብ ይገባል። ከጠላት እንደ አንዱ መሆኑንም ማወቅ አለበት።
እኛም ከማሸነፍ ውጭ ሌላ ምርጫ የለንምና በአንድነት በቁርጠኝነት በፅናት ቆመን ጠላትን ታሪክ አድርገን ማንነታችንንና ነፃነታችንን በፅኑ አለት ላይ እንገነባለን‼️