በድጋሚ ውጫሌ ገብቶ የነበረው የሕወሓት ኃይል ተደምሥሶ ወጣ | በወረባቦ ወደ ወደ ኮምቦልቻ ሊቆርጥ የተዘጋጀው ኃይልም ተወቅጧል

 

አሸባሪውና ወራሪው የሕወሓት ኃይል ከትናንት በስቲያ ወደ ንጹሃን ሕዝብ መድፎችን በመተኮስ ሕዝብን ካሸበረ በኋላ ወደ ውጫሌ ገብቶ የነበረ ቢሆንም ትናንት ጭስ አባሊማና ይስማ ንጉስ ላይ ጁንታውን የቀጠቀጡት የኢትዮጵያ ሃይሎች በድጋሚ ለሊቱን መጥተው ውጫሌን ተቆጣጥረው የነበሩትን የሕወሓት ኃይሎች እንደገና ጠራርገው በማስወጣት ውጫሌ በኢትዮጵያ ኃይሎች ስር ዳግም መግባቷን ዘ-ሐበሻ ከመከላከያው ምንጭ አረጋግጧል።

በውጫሌ ተራሮች ላይ የነበረው የሕወሓት ኃይል በአውሮፕላን ሲወቃ ያደረ ሲሆን ጁንታው ከፍተኛውን ኪሳራ ተከናንቧል። ሆኖም ግን እርጉዝ ሴት ሳይቀር ለዘረፈና ለውጊያ ያሰማራው የጁንታው ኃይል ቁጥሩ ከፍተኛ በመሆኑ በቀላሉ ሁሉንም ደምስሶ ለመጨረሰ አልተቻለም። በመሆኑንም የተቀረው ኃይል እግሬ አውጪኝ ብሎ ወደ ውርጌሳና መርሳ መፈርጠጡን የዘ-ሐበሻ ምንጭ አክለዋል።

ይህ ደላንታን እና ወገል ጤናን ካለምንም ውጊያ የተቆጣጠረው የሕወሓት ኃይል ዓላማውን ደሴና ኮምቦልቻ በማድረግ በአራት አቅጣጫ ተንቅሳቅሶ እንደነበር የሚናገሩት ምንጩ፤ በበሸሎ በኩል ወደ ኩታበር፤ በውጫሌ ሃይቅ ወደ ደሴ፣ በወረባቦ ጭፍራ፤ ከጭፍራ ወደ ተውለደሬ፤ በቢስቲማ ወደ ሐይቅ አስጢፋኖስ ከዛም መድረሻውን ደሴና ኮምቦልቻ ለማድረግ ለሊቱን ሙሉ ሲታገል ነበር ያደረው።

ዛሬ ጠዋት በወረባቦ ወረዳ በቤስቲማ አድርጎ ወደ ኮምቦልቻ ለመግባት ቋምጦ የነበረው የሕወሃት አሸባሪ ኃይል በኃይለኛው ተመቶ የኮምቦልቻ ሕልሙ ተሰናክሎበት ተመልሷል። የኢትዮጵያ አየር ኃይልም በየተራራውና በየሸጡ ተወሽቆ ያለውን እና ከባድ መሳሪያ ወደ ሕዝብ ላይ ሲተኩስ የነበረውን የጁንታ ኃይል አደባይቶታል።

በተለይም ሕወሃት በውጫሌ ወደ ሐይቅ ለመሄድና ደሴ ለመግባት በከባዱ ቋምጦ የነበበረ ቢሆንም በየተራራው የተወሸቁት ኃይሎቹ እዚያው በአውሮፕላን ድብደባ ቀርተዋል።