ሸሽቶ እንደገና ተከዜ በርሃ የገባውን ትርፍራፊ የሕወሓት ኃይል ማሳደዱ ቀጥሏል | ዕድሜያቸው 16 እስከ 18 ያሉ ታጣቂዎች እጃቸውን ለኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ሰጡ

ባለፈው ሳምንት በተለያዩ አካባቢዎች በተደረጉ ውጊያዎች ክፉኛ የተመታው ሕወሓት የተራረፈው ኃይል ሸሽቶ ተመልሶ ወደ ተከዜ በርሃ መግባቱን መዘገባችን ይታወሳል። በዚህም መሰረት መከላከያው አሁንም የተራረፈውን የሕወሃት ኃይል ማሳደዱን ቀጥሏል።

አንድ የዘ-ሐበሻ የመከላከያ ምንጭ እንደተናገሩት በዘመናዊ ጦር መሳሪያ በተጋዘ መልኩ ሌሊቱን የተራረፈው ኃይል የተሰባሰበት ተከዜ በረሃ በአየር ተደብድቧል። በዚህም ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የተራረፈው ቡድን አባላት ተደምስ ሰዋል። በዚህ የጁንታውን የተራረፈ ኃይል የማሳደድ ዘመቻም ዕድሜያቸው ከ16 እስከ 18 ያሉ ታጣቂዎች ራሳቸው እጃቸውን እንደሰጡ የሚናገሩት ምንጩ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጃቸውን እየሰጡ ካሉ የሕወሓት ተዋጊዎች ውስጥ አብዛኛው እድሜያቸው በዚህ ክልል መሆኑን ገልጸው፤ ሕወሓት ለ እድሜ ያልደረሱ ልጆችን ለጦር መስ ዋ ዕትነት ዳርጓቸዋል ብለዋል።

በሌላ በኩል በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አመራር መዋቅር ውስጥ በመሆን ከጁንታው ጋር ሲሰሩ የነበሩት ሃይሎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑ ተገልጿል።