ፖለቲካው ይደርሳል!!

አምደማርያም እዝራ

  ጎብዝ በጭልጋ በኩል የተከፈተብን ጦርነት የተቀናጀ ነው።ይህን ውጊያ አንድ ሁነን መመከት ግድ ይለናል።የወቅቱን ተጨባጭ የጠላት አሰላለፍ በመረዳት ሁሌም እንደምለው የርዕዮተ-ዓለሙ ልዩነት ይቆየን።የፖለቲካ ልዩነታችንን ማስተናገድ የምንችለው አገርና ህዝብ ሰላም ሲሆን ነው።አገርና ህዝብ ሲኖረን  ነው።አሁን አንገብጋቢው ህልውናችን ጉዳይ ነው።የህልውና ትግሉ ይቅደም እያልኩ ነው።

በጭልጋው ውጊያ ከአሸባሪው የቅማንት ኮሚቴ ጋር የተቀናጀ ጦርነት የከፈቱብን በሱዳንና በግብጽ ቅንጅት የሽብር ስልጠና ወሱደው ሰርገው የገቡት እኩዮች ናቸው።ከሽብርተኛው ቡድን መካከል በርካቶች ተደምስሰዋል።ከተደመሰሱት አሸባሪዎች ውስጥ ማንነታቸውን በጉልህ መለየት የሚያስችል መታወቂያ ተገኝቷል።ከቁስለኛው መካከልም የአሸባሪው ትህነግ ልዩ ኃይል/ትግሬዎች እና በኦሮሞ ብልጽግና ፓርቲ ባሉ አመራሮች የሚደገፈው የአሸባሪው የኦነግ ታጣቂዎች አብረው ተግኝቷል።ለዚህም ነው የተከፈተብን ጦርነት የተቀናጀ ነው እያልኩ ያለሁት።የጥምረት ነው።

ይደገም።ሰሞኑን በዋግህምራ (አበርገሌ) በኩልም ሽብርተኞቹ የሽብር ተግባር ለመፈጸም ሞክረዋል።ሙከራቸው ለአማራ ህዝብ የህይወት መስዋእትነት እየከፈለ በሚገኘው በጀግናው የአማራ ልዩ ኃይልና በዋግ ሹሞች አገር ህዝብ ተመክቷል።ድብቅ ተመትቷል።የቀረው ወደ ዋሻው ተመልሷል።ወደ ዋሻው የተመለሰው አሸባሪ ኃይል እንደ ገና አንሰራርቶ ለሽብር ተግባር መምጣቱ አይቀርም።ምክንያቱ ዓላማው ነውና።ስለሆነም በእየ አቅጣጫው አማራ በመሆናችን ብቻ የተከፈተብነን የሽብርና የጥፋት ተግባር መመከት የምንችለው ከብረት በጠነከረ አንድነት ነው።ከአለሎ በጠጠረ አድረጃጀት ነው።

በአጣዬ፣በከሚሴ… በኩል ያለው አሸባሪ አሁን ለጊዜው አሰበከ እንጂ አልተደመሰሰም።እንዲውም በኦሮሞ ብልጽግና አመራር የሚደገፈው ኦነግ ሸኔ በርካታ አዳዲስ አሸባሪዎችን ማስመረቁን እየነገረን ነው።

እናም ከግራም ከቀኝም፣ከውጭም ከውስጥም የተደቀነብነን ጥፋት ለመመከት ፍጹም አንድ የሆነ አደረጃጀት እንጂ ፖለቲካዊ ጎራ ለይቶ መጠዛጠዝ ያስፈልገናል ብዬ አላምንም።ፖለተካዊ ልዩነቱ ከህልውና ማኖር በኋላ ይደርሳልና!!

በአማራ ክልል ዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ በኒሯቅ ከተማ  የሕወሓት ሽፍታ ታጣቂዎች ጥቃት ከፍተው በሰው ሕይወት እና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሳቸዉን በትናንትናው እና ከትናትን በስቲያ ባቀረብነው የዘ-ሀበሻ 3 መረጃዎች ላይ መዘገባችን አይዘነጋም። 

የጁንታው ርዝራዥ የአማራ ልዩ እና የአካባቢው የጸጥታ አካላት ባልሸፈነው ቦታ ጨለማን ተገን በማድረግ ተመሳስሎ አበርገሌ ወረዳ ኒራቅ በመግባት 11 ንጹሃን ዜጎችን ገድለዋል። እንዲሁም ሕወሓት ድንገት በሰነዘረው ጥቃት የ4 የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ህይወት ማለፉንም የዘ-ሐበሻ ምንጭ ገልጿል። በአንጻሩ የአማራ ልዩ ኃይል በጁንታው ላይ በወሰደው እርምጃ ከ50 በላይ ታጣቂዎች መደምሰሳቸውን ነው ምንጩ የነገሩን።

ሕወሓት ከአንድ ወር በፊት በዚሁ ዞን ፃታ በተባለ አካባቢ ሕወሓት ተጨማሪ ጥቃት ሰንዝሮ ንጹሃን ዜጎችን ገድሎ፤ መድሃኒት ቤቶችን እና እህል ማጠራቀሚያዎችን ዘርፎ መሄዱ ይታወቃል።

ይህን ተከትሎም በክብር ለተሰው የአመራ ልዩ ኃይል አባላትና ንጹሃን ዜጎች በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ከተማ አስተዳደር የሃዘን መግለጫውን ዛሬ አስተላልፏል።

በዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር አበርገሌ ወረዳ ሚያዝያ 17 ቀን ለ18 /2013 ንጋት 11: 00 ሰዓት አካባቢ የጁንታው ርዝራዥ የአበርገሌ ወረዳ ማእከል በሆነችዉ ኒየረ-አቁ ከተማ ሰርጎ በመግባት ድንገት የከፈተዉን ተኩስ በአይበገሬው የአማራ ልዩ ሀይል እና በአካባቢው የጸጥታ ሀይል በተደረገዉ የመልሶ ማጥቃት ምት ጁንታዉ መቋቋም አቅቶት ክንዱ ዝሎና በየሜዳዉ ተዘርሮ እንዲሁም አይቀጡት ቅጣት ተቀጥቶ የታየ ሲሆን ትርፍራፊው ደግሞ እግሬ አዉጭኝ ብሎ ወደ ነበረበት ዋሻና ጫካ ሸሽቶ የሄደ መሆኑ ታዉቋል ።

በዚህም ህዝብ ላይ ይደርስ የነበረዉን ከፍተኛ ጉዳት የህዝብ መመኪያ የሆነው የአማራ ልዩ ሃይልና የአካባቢው ጸጥታ ሃይል ዉድ ሂወቱን ያለስስት ለህዝብ በመክፈል ህዝብን መታደግ መቻሉንና የህዝብ አሌንታ መሆኑን አረጋግጣል፡፡

በዚህ አጋጣሚ  ህዝባዊ ጀብድ ሰርተዉ መስዋእት ለሆኑ ወንድሞችና ዉድ የህዝብ ልጆች ፈጣሪ ነብሳቸዉን በአጸደ ገነት እንዲያኖርላቸው ህዝባችን ይመኛል፡፡ ሲል የአበርገሌ ከተማ አስተዳደር መጽናናትን ተመኝቷል።