ደሴ ከተማ ውስጥ የተሰገሰጉ፣ ትግል ጎታች እና ሕዝብ አሸባሪ የሕወሓት ተላላኪዎች ሊመቱ ይገባል ተባለ

 

ሕወሓት በፈጸመው ወረራ ምክንያት በርካታ ተፈናቃዮችን አስጠግታ የምትገኘው ደሴ ከተማ ውስጥ አንዳንድ የሕወሓት ቅጥረኞችና ሌቦች ሱቃችሁን ዝጉ በሚል የንግዱን ማህበረሰብ በፍርሃት ውስጥ እንዲወድ በማድረግ ላይ የሚገኙ ሲሆን በዚህ ወሬ የተነሳም የተወሰኑ ሱቆች ዛሬ ዘግተው እንደነበር ምንጮች ከደሴ ገለጹ።

የደሴ ሕዝብ ዛሬ ሕወሓትን ለመመከት ልክ እንደ ሰሞኑ ሑሉ በተጠንቀቅ በቆመበት በዚህ ሰዓት እነዚህ ሰርጎ ገብ የወያኔ ተላላኪዎች ሕዝብን ለማሸበር እየሞከሩ በመሆኑ እርምጃ ሊወሰድባቸው እንደሚገባ የአካባቢው ነዋሪዎች ለዘ-ሐበሻ መል ዕክታቸውን ልከዋል።

ይህ በ እንዲህ እንዳለም የደሴ ከተማ አስተዳደር ማምሻውን ባውወጣው ማሳሰቢያ “የደሴ ከተማ ማህበረሰብ በመረጋጋትና አካባቢውን በመደራጀት በንቃት ልንጠብቅ ይገባል።
ፀጉረ ልውጥና አጠራጣሪ ነገሮችን ስናይ ከፀጥታ አከላት ጋር በመሆን ልንጠቁም ይገባል።
አካባቢውን በንቃት በመጠበቅና የከተማውን ሰላም ለማስከበር እያደረገ ያለው ንቁ ተሳትፎ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል።”