የኢትዮጵያ አየር ኃይሎች በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ የሚገኝ ወታደራዊ ስትራቴጂካዊ ቦታን ማውደማቸው ተገለጸ

የተመረጡ ወታደራዊ ኢላማዎችን ብቻ በተሳካ ሁኔታ በመምታታቸው የአየር ስናይፐሮቹ የሚል ስያሜ የወጣላቸው የኢትዮጵያ አየር ኃይሎች በዛሬው ዕለት በመቀሌ ከተማ የሚገኝ ወታደራዊ ስትራቴጂካዊ ቦታን ማውደማቸው ተገለጸ።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ዛሬ ጥቅምት 18/2014 ዓ.ም ረፋድ ላይ በመቐለ የተመረጡ የአሸባሪ ህወሓት ወታደራዊ ቤዞችን የመታው።

መቐለ ከተማ እና ዙርያዋ ከደርዘን በላይ የአሸባሪ ህወሓት ወታደራዊ ቢዝ እንዳለው የሚታወቅስ ሲሆን ስናይፐሩ የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአሸባሪው ቤዞች ብቻ ነጥሎ በመምታት ብቃቱን አሳይቷል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል።

ዛሬ የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታርጌት ያደረገው በመቀሎእ የሚገኘውን መስፍን ኢንጅነሪንግ ሁለተኛው ክፍል ሲሆን ይህ መስፍን ኢንጅነሪንግ ሁለተኛው ክፍል ሕወሃት ወታደራዊ መሣሪያዎችን የሚጠግንበት ቦታ እንደሆነ ተገልጿል። በተጨማሪም ለወታደራዊ ትራንስፖርት የሚሆኑ እቃዎችንም እዚህ እንደሚያከማች ይነገራል።