ላምሮት ከማል ላይ የጠቅላይ ፍርድቤት ይግባኝ ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳን ገላን ኮንዶሚኒዬም በመውሰድ የግድያ ቦታ አመቻችታለች ተብላ የተከሰሰችው ላምሮት ከማል ላይ የጠቅላይ ፍርድቤት ይግባኝ ክርክር ለማድረግ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ፡፡

Lamrot Kemal


ተለዋጭ ቀጠሮውን የሰጠው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት 2ኛ ይግባኝ ሰሚ ችሎት ነው፡፡


በተከሳሿ ላይ ከአንድ ወር በፊት የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 2ኛ የፀረሽብርና የህገመንግስት ጉዳዮች ወንጀል ችሎት በዓቃቢህግ የቀረበ ማስረጃ ለወንጀሉ መፈፀም አስረጂ አደለም ሲል በነጻ አሰናብቷት የነበረ ሲሆን፡
ዓቃቢህግ በብይኑ ቅር በሰኘት ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ይግባኝ አቅርቧል፡፡
ይግባኝ ሰሚ ችሎቱም ይግባኙ ያስቀርባል ወይስ አያስቀርብም የሚለውን መርምሮ ያስቀርባል በማለት ለተከሳሿ ባለችበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት መጥሪያ እንዲደርሳት ተደርጓል፡፡
በዛሬው ቀጠሮ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት በመብራት ባለመኖሩና ተጠርጣሪዋ መጥሪያ ሲደርሳት እኔም በፕላዝማ ተገኝቼ ሀሳቤን ላቅርብ በማለቷን ተከትሎ እንዲሁን ተከላካይ ጠበቃዋ በችሎት መደራረብ ምክንያት ማረሚያ ቤት ሄጄ ደንበኛዬን ማግኘት አልቻልኩም በማለቱ ምክንያት ፍርድ ቤቱ የተከሳሿ ሀሳብ መደመጥ አለበት ሲል ለቃል ክርክር ለማድረግ ለሰኔ 9 ቀን 2013 ዓ /ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰቷል፡፡
ተከሳሿ በሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ/ም በአዲስ አበባ ገላን ኮንዶሚኒዬም አካባቢ በሽጉጥ ተመቶ ህይወቱ ያለፈውን አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ በተመለከተ ከአንድ የሸኔ አመራር ጋር በሜክሲኮ አካባቢ በመገናኘት ተልኮ ተቀብላ ሀጫሉን ወንጀሉ ወደ ተፈፀመ ቦታ በመውሰድ ግድያውን አመቻችታለች ተብላ መከሰሷ ይታወሳል፡፡
ጋዜጠኛ ታሪክ አዱኛ